1
የማቴዎስ ወንጌል 16:24
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፤ “እኔን መከተል የሚፈልግ ራሱን ይካድ፤ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ።
နှိုင်းယှဉ်
የማቴዎስ ወንጌል 16:24ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
2
የማቴዎስ ወንጌል 16:18
እኔም እንዲህ እልሃለሁ፤ አንተ (ጴጥሮስ)፥ አለት ነህ፤ በዚህችም የመሠረት ድንጋይ ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፤ ይህችንም ቤተ ክርስቲያን የሞት ኀይል እንኳ አያሸንፋትም።
የማቴዎስ ወንጌል 16:18ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
3
የማቴዎስ ወንጌል 16:19
እነሆ፥ ለአንተ የሰማይ መንግሥትን መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፤ በምድር ያሰርከው በሰማይ የታሰረ ይሆናል፤ በምድር የፈታኸው በሰማይ የተፈታ ይሆናል።”
የማቴዎስ ወንጌል 16:19ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
4
የማቴዎስ ወንጌል 16:25
ሕይወቱን ለማዳን የሚፈልግ ሁሉ ያጠፋታል፤ ሕይወቱን ስለ እኔ የሚያጠፋት ግን ያገኛታል።
የማቴዎስ ወንጌል 16:25ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
5
የማቴዎስ ወንጌል 16:26
ሰው የዓለሙን ሁሉ ሀብት ቢያገኝ፥ ነፍሱን ግን ቢያጠፋ፥ ምን ይጠቅመዋል? ወይስ ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ዋጋ ሊከፍል ይችላል?
የማቴዎስ ወንጌል 16:26ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
6
የማቴዎስ ወንጌል 16:15-16
ኢየሱስም “እናንተስ እኔን ማን ትሉኛላችሁ?” አላቸው። በዚያን ጊዜ ስምዖን ጴጥሮስ፦ “አንተ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ መሲሕ ነህ፤” ሲል መለሰለት።
የማቴዎስ ወንጌል 16:15-16ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
7
የማቴዎስ ወንጌል 16:17
ኢየሱስም እንዲህ አለው፦ “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ! የተባረክህ ነህ! ይህን የገለጠልህ በሰማይ ያለው አባቴ ነው እንጂ ሰው አይደለም።
የማቴዎስ ወንጌል 16:17ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
ပင်မစာမျက်နှာ
သမ္မာကျမ်းစာ
အစီအစဉ်များ
ဗီဒီယိုများ