1
ኦሪት ዘፍጥረት 15:6
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
አብራም በእግዚአብሔር አመነ፤ እምነቱም ጽድቅ ሆኖ ተቈጠረለት።
နှိုင်းယှဉ်
ኦሪት ዘፍጥረት 15:6ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
2
ኦሪት ዘፍጥረት 15:1
ከዚህ በኋላ አብራም ራእይ አየ፤ እግዚአብሔርም “አብራም፥ አትፍራ፤ እንደ ጋሻ ሆኜ ከአደጋ ሁሉ እጠብቅሃለሁ፤ ታላቅ በረከትም እሰጥሃለሁ” ሲል ሰማው።
ኦሪት ዘፍጥረት 15:1ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
3
ኦሪት ዘፍጥረት 15:5
ቀጥሎም እግዚአብሔር አብራምን ወደ ውጪ አወጣውና “ወደ ሰማይ ተመልከት፤ ከዋክብትን መቊጠር ትችል እንደሆን ሞክር፤ እንግዲህ የአንተም ዘሮች እንደዚህ ይበዛሉ” አለው።
ኦሪት ዘፍጥረት 15:5ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
4
ኦሪት ዘፍጥረት 15:4
ከዚህ በኋላ የእግዚአብሔር ቃል “ይህ ኤሊዔዘር የተባለው አገልጋይ የአንተን ሀብት አይወርስም፤ ከአንተ የሚወለደው ልጅ ወራሽህ ይሆናል” ብሎ ሲነግረው ሰማ።
ኦሪት ዘፍጥረት 15:4ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
5
ኦሪት ዘፍጥረት 15:13
እግዚአብሔር አብራምን እንዲህ አለው፦ “የልጅ ልጆችህ በባዕድ አገር ስደተኞች እንደሚሆኑ ዕወቅ፤ እዚያም በባርነትና በጭቈና ለአራት መቶ ዓመት ያስጨንቁአቸዋል፤
ኦሪት ዘፍጥረት 15:13ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
6
ኦሪት ዘፍጥረት 15:2
አብራምም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ጌታ አምላክ ሆይ፥ ምንም ልጅ ስለሌለኝ የምትሰጠኝ በረከት ምን ያደርግልኛል? ሀብቴን የሚወርሰው የደማስቆ ሰው የሆነው ኤሊዔዘር ነው።
ኦሪት ዘፍጥረት 15:2ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
7
ኦሪት ዘፍጥረት 15:18
በዚያን ዕለት እግዚአብሔር ለአብራም እንዲህ በማለት ቃል ኪዳን ገባለት፦ “ከግብጽ ወንዝ ጀምሮ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ያለውን ምድር ሁሉ ለዘሮችህ እሰጣለሁ፤
ኦሪት ዘፍጥረት 15:18ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
8
ኦሪት ዘፍጥረት 15:16
የልጅ ልጆችህ ወደዚህ ተመልሰው የሚመጡት በአራተኛው ትውልድ ነው፤ እስከዚያ የሚቈዩበትም ምክንያት የአሞራውያን ኃጢአት ገና ስላልተፈጸመ ነው።”
ኦሪት ዘፍጥረት 15:16ရှာဖွေလေ့လာလိုက်ပါ။
ပင်မစာမျက်နှာ
သမ္မာကျမ်းစာ
အစီအစဉ်များ
ဗီဒီယိုများ