1
የማርቆስ ወንጌል 13:13
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መቅካእኤ
በእኔ ምክንያት በሰው ሁሉ ዘንድ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ፤ እስከ መጨረሻው የሚጸና ግን ይድናል።
ႏွိုင္းယွဥ္
የማርቆስ ወንጌል 13:13ရွာေဖြေလ့လာလိုက္ပါ။
2
የማርቆስ ወንጌል 13:33
ስለዚህ ጊዜው መቼ እንደሚሆን አታውቁምና ተጠንቀቁ፤ ትጉ፥ ጸልዩም።
የማርቆስ ወንጌል 13:33ရွာေဖြေလ့လာလိုက္ပါ။
3
የማርቆስ ወንጌል 13:11
ተይዛችሁ ለፍርድ በምትቀርቡበት ጊዜ፥ በዚያች ሰዓት የሚሰጣችሁን ተናገሩ እንጂ ምን እንናገራለን በማለት አስቀድማችሁ አትጨነቁ፤ የሚናገረው መንፈስ ቅዱስ እንጂ እናንተ አይደላችሁምና።
የማርቆስ ወንጌል 13:11ရွာေဖြေလ့လာလိုက္ပါ။
4
የማርቆስ ወንጌል 13:31
ሰማይና ምድር ያልፋሉ፥ ቃሌ ግን አያልፍም።
የማርቆስ ወንጌል 13:31ရွာေဖြေလ့လာလိုက္ပါ။
5
የማርቆስ ወንጌል 13:32
ነገር ግን ስለዚያች ቀን ወይም ስለዚያችም ሰዓት ከአብ በቀር፥ የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ፥ ወልድም ቢሆን፥ ማንም አያውቅም።
የማርቆስ ወንጌል 13:32ရွာေဖြေလ့လာလိုက္ပါ။
6
የማርቆስ ወንጌል 13:7
ስለ ጦርነትና ስለ ጦርነት ወሬ በምትሰሙበት ጊዜ አትደንግጡ፤ ይህማ መሆን አለበት፤ ፍጻሜው ግን ገና ነው።
የማርቆስ ወንጌል 13:7ရွာေဖြေလ့လာလိုက္ပါ။
7
የማርቆስ ወንጌል 13:35-37
እንግዲህ የቤቱ ባለቤት በምሽት ወይም በውድቅት፥ በዶሮ ጩኸት ወይም ጎሕ ሲቀድ እንደሚመጣ አታውቁምና ተግታችሁ ጠብቁ፤ ድንገት ሲመጣ ተኝታችሁ እንዳያገኛችሁ ለእናንተ የምነግራችሁን ለሰው ሁሉ እናገራለሁ፤ ተግታችሁ ጠብቁ።
የማርቆስ ወንጌል 13:35-37ရွာေဖြေလ့လာလိုက္ပါ။
8
የማርቆስ ወንጌል 13:8
ሕዝብ በሕዝብ ላይ፥ መንግሥት በመንግሥት ላይ ይነሣል፤ በብዙ ቦታም የመሬት መንቀጥቀጥና ራብ ይሆናል፤ እነዚህ ሁሉ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው።
የማርቆስ ወንጌል 13:8ရွာေဖြေလ့လာလိုက္ပါ။
9
የማርቆስ ወንጌል 13:10
አስቀድሞ ግን ወንጌል ለሕዝብ ሁሉ መሰበክ አለበት።
የማርቆስ ወንጌል 13:10ရွာေဖြေလ့လာလိုက္ပါ။
10
የማርቆስ ወንጌል 13:6
ብዙዎች፥ “እኔ እርሱ ነኝ” እያሉ በስሜ ይመጣሉ፤ ብዙዎችንም ያስታሉ።
የማርቆስ ወንጌል 13:6ရွာေဖြေလ့လာလိုက္ပါ။
11
የማርቆስ ወንጌል 13:9
ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፤ ለሸንጎ አሳልፈው ይሰጧችኋል፤ በምኵራብ ይገርፏችኋል፤ ምስክር ትሆኑም ዘንድ በእኔ ምክንያት በገዢዎችና በነገሥታት ፊት ትቆማላችሁ።
የማርቆስ ወንጌል 13:9ရွာေဖြေလ့လာလိုက္ပါ။
12
የማርቆስ ወንጌል 13:22
ሐሰተኛ ክርስቶሶችና ሐሰተኛ ነቢያት ተነሥተው፥ ምልክቶችንና ድንቆችን በማድረግ፥ ቢቻላቸው የተመረጡትን እንኳ ያስታሉ።
የማርቆስ ወንጌል 13:22ရွာေဖြေလ့လာလိုက္ပါ။
13
የማርቆስ ወንጌል 13:24-25
በዚያን ጊዜ፥ ከመከራው በኋላ ፀሓይ ትጨልማለች፥ ጨረቃም ብርሃኗን አትሰጥም፤ ከዋክብት ከሰማይ ይረግፋሉ፤ የሰማይ ኀይላትም ይናወጣሉ።
የማርቆስ ወንጌል 13:24-25ရွာေဖြေလ့လာလိုက္ပါ။
ပင္မစာမ်က္ႏွာ
သမၼာက်မ္းစာ
အစီအစဥ္မ်ား
ဗီဒီယိုမ်ား