1
ኦሪት ዘፍጥረት 25:23
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መቅካእኤ
ጌታም እንዲህ አላት፥ “ሁለት ሕዝቦች በማሕፀንሽ አሉ፤ ሁለቱም ወገኖች ከውስጥሽ ተለያይተው ይወጣሉ፤ አንዱም ከሌላው ይበረታል፤ ታላቁም ለታናሹ አገልጋይ ይሆናል።”
താരതമ്യം
ኦሪት ዘፍጥረት 25:23 പര്യവേക്ഷണം ചെയ്യുക
2
ኦሪት ዘፍጥረት 25:30
ዔሳውም ያዕቆብን፥ “ከዚህ ከቀዩ ወጥ አብላኝ፥ እኔ እጅግ እርቦኛልና!” አለው፤ (ኤዶም የተባለውም በዚህ ምክንያት ነበር።)
ኦሪት ዘፍጥረት 25:30 പര്യവേക്ഷണം ചെയ്യുക
3
ኦሪት ዘፍጥረት 25:21
ርብቃ መኻን ስለ ነበረች ይስሐቅ ስለ እርሷ ወደ ጌታ ጸለየ፤ ጌታም ጸሎቱን ስለ ሰማ ርብቃ ፀነሰች፤
ኦሪት ዘፍጥረት 25:21 പര്യവേക്ഷണം ചെയ്യുക
4
ኦሪት ዘፍጥረት 25:32-33
ዔሳውም “እኔ መሞቴ ነው፤ ታዲያ ብኲርና ምን ያደርግልኛል?” አለው። ያዕቆብም፥ “እስኪ በቅድሚያ ማልልኝ” አለው። ስለዚህ ዔሳው ምሎ ብኲርናውን ለያዕቆብ ሸጠ።
ኦሪት ዘፍጥረት 25:32-33 പര്യവേക്ഷണം ചെയ്യുക
5
ኦሪት ዘፍጥረት 25:26
ከዚያም በኋላ ወንድሙ ወጣ፥ በእጁም የዔሳውን ተረከዝ ይዞ ነበር፤ ስለዚህ ስሙ ያዕቆብ ተባለ። ልጆቹን በወለደች ጊዜ ይስሐቅ ሥልሳ ዓመት ሆኖት ነበር።
ኦሪት ዘፍጥረት 25:26 പര്യവേക്ഷണം ചെയ്യുക
6
ኦሪት ዘፍጥረት 25:28
ይስሐቅም ዔሳው ካደነው ይበላ ነበርና ይወደው ነበር፥ ርብቃ ግን ያዕቆብን ትወድ ነበር።
ኦሪት ዘፍጥረት 25:28 പര്യവേക്ഷണം ചെയ്യുക
ആദ്യത്തെ സ്ക്രീൻ
വേദപുസ്തകം
പദ്ധതികൾ
വീഡിയോകൾ