1
ኦሪት ዘፍጥረት 17:1
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
አማ2000
ከዚህም በኋላ አብራም የዘጠና ዘጠኝ ዓመት ሰው በሆነ ጊዜ እግዚአብሔር ለአብራም ተገለጠለት፤ እንዲህም አለው “በፊትህ የሄድሁ ፈጣሪህ እግዚአብሔር እኔ ነኝ፤ በፊቴ መልካም አድርግ፤ ንጹሕም ሁን፤
Mampitaha
Mikaroka ኦሪት ዘፍጥረት 17:1
2
ኦሪት ዘፍጥረት 17:5
እንግዲህ ስምህ አብራም አይባልም ‘አብርሃም’ ይባላል እንጂ፤ ለብዙ አሕዛብ አባት አድርጌሃለሁና።
Mikaroka ኦሪት ዘፍጥረት 17:5
3
ኦሪት ዘፍጥረት 17:7
ቃል ኪዳኔንም በእኔና በአንተ መካከል፥ ከአንተም በኋላ በዘርህ መካከል በትውልዳቸው ለዘለዓለም ኪዳን አቆማለሁ፤ ለአንተና ከአንተም በኋላ ለዘርህ አምላክ እሆን ዘንድ።
Mikaroka ኦሪት ዘፍጥረት 17:7
4
ኦሪት ዘፍጥረት 17:4
“እነሆ፥ ቃል ኪዳኔን በእኔና በአንተ መካከል አጸናለሁ፤ ለብዙ አሕዛብም አባት ትሆናለህ።
Mikaroka ኦሪት ዘፍጥረት 17:4
5
ኦሪት ዘፍጥረት 17:19
እግዚአብሔርም አብርሃምን አለው፥ “እሺ እነሆ፥ ሚስትህ ሣራ ወንድ ልጅን ትወልድልሃለች፤ ስሙንም ይስሐቅ ብለህ ትጠራዋለህ፤ ለእርሱና ከእርሱ በኋላ ለዘሩ አምላክ እሆን ዘንድ ቃል ኪዳኔን ለዘለዓለም ቃል ኪዳን ከእርሱ ጋር አቆማለሁ።
Mikaroka ኦሪት ዘፍጥረት 17:19
6
ኦሪት ዘፍጥረት 17:8
በውስጥዋ የምትኖርባትን ይህችን ምድር፥ የከነዓንን ምድር ሁሉ፥ ለዘለዓለም ይገዙአት ዘንድ ለዘርህ እሰጣለሁ፤ አምላክም እሆናቸዋለሁ።”
Mikaroka ኦሪት ዘፍጥረት 17:8
7
ኦሪት ዘፍጥረት 17:17
አብርሃምም በግንባሩ ወደቀ፤ ሳቀም፤ በልቡም እንዲህ ብሎ አሰበ፥ “የመቶ ዓመት ሰው ስሆን በውኑ እኔ ልጅ እወልዳለሁን? ዘጠና ዓመት የሆናትም ሣራ ትወልዳለችን?”
Mikaroka ኦሪት ዘፍጥረት 17:17
8
ኦሪት ዘፍጥረት 17:15
እግዚአብሔርም አብርሃምን አለው፥ “ሚስትህ ሦራ እንግዲህ ሦራ ተብላ አትጠራም፤ ስምዋ ‘ሣራ’ ይሆናል እንጂ።
Mikaroka ኦሪት ዘፍጥረት 17:15
9
ኦሪት ዘፍጥረት 17:11
የሰውነታችሁን ቍልፈት ትገረዛላችሁ፤ በእኔና በእናንተ መካከል ላለውም ቃል ኪዳን ምልክት ይሆናል።
Mikaroka ኦሪት ዘፍጥረት 17:11
10
ኦሪት ዘፍጥረት 17:21
ቃል ኪዳኔን ግን በሚመጣው ዓመት በዚሁ ጊዜ ሣራ ከምትወልድልህ ከይስሐቅ ጋር አቆማለሁ።”
Mikaroka ኦሪት ዘፍጥረት 17:21
11
ኦሪት ዘፍጥረት 17:12-13
ሕፃኑንም በስምንተኛው ቀን ትገርዙታላችሁ፤ በቤት የተወለደ ወይም ከዘራችሁ ያይደለ፥ በብርም ከእንግዳ ሰው የተገዛ ወንድ ሁሉ በትውልዳችሁ ይገረዝ። በቤትህም የተወለደ፥ በብርም የተገዛ ፈጽሞ ይገረዝ። ቃል ኪዳኔም በሥጋችሁ የዘለዓለም ቃል ኪዳን ይሆናል።
Mikaroka ኦሪት ዘፍጥረት 17:12-13
Fidirana
Baiboly
Planina
Horonan-tsary