1
ወደ ሮም ሰዎች 8:28
መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)
አማ54
እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን።
Kokisana
Luka ወደ ሮም ሰዎች 8:28
2
ወደ ሮም ሰዎች 8:38-39
ሞት ቢሆን፥ ሕይወትም ቢሆን፥ መላእክትም ቢሆኑ፥ ግዛትም ቢሆን፥ ያለውም ቢሆን፥ የሚመጣውም ቢሆን፥ ኃይላትም ቢሆኑ፥ ከፍታም ቢሆን፥ ዝቅታም ቢሆን፥ ልዩ ፍጥረትም ቢሆን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ካለ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን እንዳይችል ተረድቼአለሁ።
Luka ወደ ሮም ሰዎች 8:38-39
3
ወደ ሮም ሰዎች 8:26
እንዲሁም ደግሞ መንፈስ ድካማችንን ያግዛል፤ እንዴት እንድንጸልይ እንደሚገባን አናውቅምና፥ ነገር ግን መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል፤
Luka ወደ ሮም ሰዎች 8:26
4
ወደ ሮም ሰዎች 8:31
እንግዲህ ስለዚህ ነገር ምን እንላለን? እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል?
Luka ወደ ሮም ሰዎች 8:31
5
ወደ ሮም ሰዎች 8:1
እንግዲህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኵነኔ የለባቸውም።
Luka ወደ ሮም ሰዎች 8:1
6
ወደ ሮም ሰዎች 8:6
ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነውና፥ ስለ መንፈስ ማሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው።
Luka ወደ ሮም ሰዎች 8:6
7
ወደ ሮም ሰዎች 8:37
በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን።
Luka ወደ ሮም ሰዎች 8:37
8
ወደ ሮም ሰዎች 8:18
ለእኛም ይገለጥ ዘንድ ካለው ክብር ጋር ቢመዛዘን የአሁኑ ዘመን ሥቃይ ምንም እንዳይደለ አስባለሁ።
Luka ወደ ሮም ሰዎች 8:18
9
ወደ ሮም ሰዎች 8:35
ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ፥ ወይስ ጭንቀት፥ ወይስ ስደት፥ ወይስ ራብ፥ ወይስ ራቁትነት፥ ወይስ ፍርሃት፥ ወይስ ሰይፍ ነውን?
Luka ወደ ሮም ሰዎች 8:35
10
ወደ ሮም ሰዎች 8:27
ልብንም የሚመረምረው የመንፈስ አሳብ ምን እንደ ሆነ ያውቃል፥ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ስለ ቅዱሳን ይማልዳልና።
Luka ወደ ሮም ሰዎች 8:27
11
ወደ ሮም ሰዎች 8:14
በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸውና።
Luka ወደ ሮም ሰዎች 8:14
12
ወደ ሮም ሰዎች 8:5
እንደ ሥጋ ፈቃድ የሚኖሩ የሥጋን ነገር ያስባሉና፥ እንደ መንፈስ ፈቃድ የሚኖሩ ግን የመንፈስን ነገር ያስባሉ።
Luka ወደ ሮም ሰዎች 8:5
13
ወደ ሮም ሰዎች 8:32
ለገዛ ልጁ ያልራራለት ነገር ግን ስለ ሁላችን አሳልፎ የሰጠው ያው ከእርሱ ጋር ደግሞ ሁሉን ነገር እንዲያው እንዴት አይሰጠንም?
Luka ወደ ሮም ሰዎች 8:32
14
ወደ ሮም ሰዎች 8:16-17
የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ያ መንፈስ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክራል። ልጆች ከሆንን ወራሾች ደግሞ ነን፤ ማለት የእግዚአብሔር ወራሾች ነን፥ አብረንም ደግሞ እንድንከብር አብረን መከራ ብንቀበል ከክርስቶስ ጋር አብረን ወራሾች ነን።
Luka ወደ ሮም ሰዎች 8:16-17
15
ወደ ሮም ሰዎች 8:7
ስለ ሥጋ ማሰብ በእግዚአብሔር ዘንድ ጥል ነውና፤ ለእግዚአብሔር ሕግ አይገዛምና፥ መገዛትም ተስኖታል፤
Luka ወደ ሮም ሰዎች 8:7
16
ወደ ሮም ሰዎች 8:19
የፍጥረት ናፍቆት የእግዚአብሔርን ልጆች መገለጥ ይጠባበቃልና።
Luka ወደ ሮም ሰዎች 8:19
17
ወደ ሮም ሰዎች 8:22
ፍጥረት ሁሉ እስከ አሁን ድረስ አብሮ በመቃተትና በምጥ መኖሩን እናውቃለንና።
Luka ወደ ሮም ሰዎች 8:22
Ndako
Biblia
Bibongiseli
Bavideo