ኦሪት ዘጸአት መግቢያ

መግቢያ
ኦሪት ዘጸአት የሚዘረዝረው የእስራኤል ሕዝብ በባርነት ይኖርበት ከነበረው ከግብጽ ምድር ስለ መውጣቱ ሁኔታ ነው፤ መጽሐፉ ሦስት ዋና ዋና ክፍሎች አሉት፦
1. ዕብራውያን ነጻ ስለ መውጣታቸውና ወደ ሲና ተራራ ስላደረጉት ጒዞ ይናገራል።
2. እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር ቃል ኪዳን ስለ መግባቱና የሥነ ምግባር፥ የመተዳደሪያና የሃይማኖት ሕጎችን ለእነርሱ ስለ መስጠቱ ይናገራል።
3. ለእስራኤል፥ እንዲሁም ለካህናት ተግባርና ለእግዚአብሔር አምልኮ ስለ ተሰጡት ሕጎች ይናገራል።
ከሁሉም በላይ ይህ መጽሐፍ የሚያስረዳው እግዚአብሔር በባርነት ይኖሩ የነበሩትን ሕዝቡን ነጻ ካወጣ በኋላ፥ ለወደፊቱ ተስፋ ያላቸው ሕዝብ እንዲሆኑ እንዴት ይሠራ እንደ ነበር ነው።
በመጽሐፉ ውስጥ የጐላ ባለታሪክ ሆኖ የቀረበው ሰብአዊ ፍጡር፥ ሕዝቡን ከግብጽ እንዲያወጣለት እግዚአብሔር የመረጠው ሰው ሙሴ ነው፤ ከመጽሐፉ በጣም የታወቀው ክፍል ዐሥሩ ትእዛዞች የተዘረዘሩበት ምዕራፍ 20 ነው።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
የእስራኤል ከግብጽ ነጻ መውጣት 1፥1—15፥21
ሀ. ባርነት በግብጽ 1፥1-22
ለ. የሙሴ ልደትና ዕድገት 2፥1—4፥31
ሐ. ሙሴና አሮን በፈርዖን ፊት 5፥1—11፥10
መ. ፋሲካና ከግብጽ መውጣት 12፥1—15፥21
ከቀይ ባሕር እስከ ሲና ተራራ 15፥22—18፥27
ሕግና ቃል ኪዳን 19፥1—24፥18
የተቀደሰው ድንኳንና የአምልኮ ሥርዓት 25፥1—40፥38

하이라이트

공유

복사

None

모든 기기에 하이라이트를 저장하고 싶으신가요? 회원가입 혹은 로그인하세요