ትንቢተ አብድዩ መግቢያ

መግቢያ
ይህ አጭር መጽሐፍ የተገኘው ኢየሩሳሌም ከክርስቶስ ልደት በፊት በ 586 ዓመት ከፈረሰች በኋላ በውል ባልታወቀ ጊዜ ውስጥ ነው፤ በዚያን ጊዜ በደቡባዊ ምሥራቅ የምትገኘውና የይሁዳ የረጅም ጊዜ ጠላት የሆነችው ኤዶም በኢየሩሳሌም መፍረስ በመደሰትና ወራሪውን በመርዳት የከተማይቱን ንብረት በመዝረፍ ላይ ነበረች። አብድዩ፥ ኤዶም ከሌሎቹ የእስራኤል ጠላቶች ጋር በመሆን ብርቱ ቅጣትና ሽንፈት እንደሚደርስባት ትንቢት ተናገረ።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
1. የኤዶም ትዕቢትና ቅጣት (1-9)
2. የኤዶም ጭካኔ (10-14)
3. የእስራኤል ድል (15-21)

Áherslumerki

Deildu

Afrita

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in