1
የማቴዎስ ወንጌል 5:15-16
መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)
አማ54
መብራትንም አብርተው ከዕንቅብ በታች አይደለም እንጂ በመቅረዙ ላይ ያኖሩታል በቤት ላሉት ሁሉም ያበራል። መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ።
Bera saman
Njòttu የማቴዎስ ወንጌል 5:15-16
2
የማቴዎስ ወንጌል 5:14
እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ። በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሰወር አይቻላትም።
Njòttu የማቴዎስ ወንጌል 5:14
3
የማቴዎስ ወንጌል 5:8
ልበ ንጹሖች ብፁዓን ናቸው፥ እግዚአብሔርን ያዩታልና።
Njòttu የማቴዎስ ወንጌል 5:8
4
የማቴዎስ ወንጌል 5:6
ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ብፁዓን ናቸው፥ ይጠግባሉና።
Njòttu የማቴዎስ ወንጌል 5:6
5
የማቴዎስ ወንጌል 5:44-45
እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፥ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፥ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤ እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፥ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና።
Njòttu የማቴዎስ ወንጌል 5:44-45
6
የማቴዎስ ወንጌል 5:3
በመንፈስ ድሆች የሆኑ ብፁዓን ናቸው፥ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና።
Njòttu የማቴዎስ ወንጌል 5:3
7
የማቴዎስ ወንጌል 5:9
የሚያስተራርቁ ብፁዓን ናቸው፥ የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉና።
Njòttu የማቴዎስ ወንጌል 5:9
8
የማቴዎስ ወንጌል 5:4
የሚያዝኑ ብፁዓን ናቸው፥ መፅናናትን ያገኛሉና።
Njòttu የማቴዎስ ወንጌል 5:4
9
የማቴዎስ ወንጌል 5:10
ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብፁዓን ናቸው፥ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና።
Njòttu የማቴዎስ ወንጌል 5:10
10
የማቴዎስ ወንጌል 5:7
የሚምሩ ብፁዓን ናቸው፥ ይማራሉና።
Njòttu የማቴዎስ ወንጌል 5:7
11
የማቴዎስ ወንጌል 5:11-12
ሲነቅፉአችሁና ሲያሳድዱአችሁ በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብፁዓን ናችሁ። ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ፥ ሐሴትም አድርጉ፤ ከእናንተ በፊት የነበሩትን ነቢያትን እንዲሁ አሳድደዋቸዋልና።
Njòttu የማቴዎስ ወንጌል 5:11-12
12
የማቴዎስ ወንጌል 5:5
የዋሆች ብፁዓን ናቸው፥ ምድርን ይወርሳሉና።
Njòttu የማቴዎስ ወንጌል 5:5
13
የማቴዎስ ወንጌል 5:13
እናንተ የምድር ጨው ናችሁ፤ ጨው አልጫ ቢሆን ግን በምን ይጣፍጣል? ወደ ውጭ ተጥሎ በሰው ከመረገጥ በቀር ወደ ፊት ለምንም አይጠቅምም።
Njòttu የማቴዎስ ወንጌል 5:13
14
የማቴዎስ ወንጌል 5:48
እንግዲህ የሰማዩ አባታችሁ ፍጹም እንደ ሆነ እናንተ ፍጹማን ሁኑ።
Njòttu የማቴዎስ ወንጌል 5:48
15
የማቴዎስ ወንጌል 5:37
ነገር ግን ቃላችሁ አዎን አዎን ወይም አይደለም አይደለም ይሁን፤ ከነዚህም የወጣ ከክፉው ነው።
Njòttu የማቴዎስ ወንጌል 5:37
16
የማቴዎስ ወንጌል 5:38-39
ዓይን ስለ ዓይን ጥርስም ስለ ጥርስ እንደ ተባለ ሰምታችኋል። እኔ ግን እላችኋለሁ፥ ክፉውን አትቃወሙ፤ ዳሩ ግን ቀኝ ጉንጭህን በጥፊ ለሚመታህ ሁሉ ሁለተኛውን ደግሞ አዙርለት፤
Njòttu የማቴዎስ ወንጌል 5:38-39
17
የማቴዎስ ወንጌል 5:29-30
ቀኝ ዓይንህም ብታሰናክልህ አውጥተህ ከአንተ ጣላት፤ ሙሉ ሰውነትህ በገሃነም ከሚጣል ይልቅ ከአካላትህ አንድ ቢጠፋ ይሻልሃልና። ቀኝ እጅህም ብታሰናክልህ ቆርጠህ ከአንተ ጣላት፤ ሙሉ ሰውነትህ በገሃነም ከሚጣል ይልቅ ከአካላትህ አንድ ቢጠፋ ይሻላልና።
Njòttu የማቴዎስ ወንጌል 5:29-30
Heim
Biblía
Áætlanir
Myndbönd