1
የማቴዎስ ወንጌል 6:33
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
አማ2000
ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል።
Bera saman
Njòttu የማቴዎስ ወንጌል 6:33
2
የማቴዎስ ወንጌል 6:34
“ነገ ለራሱ ይጨነቃልና ለነገ አትጨነቁ፤ ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል።
Njòttu የማቴዎስ ወንጌል 6:34
3
የማቴዎስ ወንጌል 6:25
“ስለዚህ እላችኋለሁ፤ ስለ ነፍሳችሁ በምትበሉትና በምትጠጡት፥ ወይም ስለ ሰውነታችሁ በምትለብሱት አትጨነቁ፤ ነፍስ ከመብል ሰውነትም ከልብስ አይበልጥምን?
Njòttu የማቴዎስ ወንጌል 6:25
4
የማቴዎስ ወንጌል 6:6
አንተ ግን ስትጸልይ፥ ወደ እልፍኝህ ግባ፤ መዝጊያህንም ዘግተህ በስውር ላለው አባትህ ጸልይ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል።
Njòttu የማቴዎስ ወንጌል 6:6
5
የማቴዎስ ወንጌል 6:9-10
እንግዲህ እናንተስ እንዲህ ጸልዩ ‘በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ! ስምህ ይቀደስ፤ መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን፤
Njòttu የማቴዎስ ወንጌል 6:9-10
6
የማቴዎስ ወንጌል 6:11
የዕለት እንጀራችንን ዛሬ ስጠን፤
Njòttu የማቴዎስ ወንጌል 6:11
7
የማቴዎስ ወንጌል 6:12
እኛም ደግሞ የበደሉንን ይቅር እንደምንል በደላችንን ይቅር በለን፤
Njòttu የማቴዎስ ወንጌል 6:12
8
የማቴዎስ ወንጌል 6:13
ከክፉም አድነን እንጂ ወደ ፈተና አታግባን፤ መንግሥት ያንተ ናትና ኃይልም ክብርም ለዘለዓለሙ፤ አሜን።’
Njòttu የማቴዎስ ወንጌል 6:13
9
የማቴዎስ ወንጌል 6:14
ለሰዎች ኀጢአታቸውን ይቅር ብትሉ፥ የሰማዩ አባታችሁ እናንተን ደግሞ ይቅር ይላችኋልና፤
Njòttu የማቴዎስ ወንጌል 6:14
10
የማቴዎስ ወንጌል 6:26
ወደ ሰማይ ወፎች ተመልከቱ፤ አይዘሩም አያጭዱምም በጎተራም አይከቱም፤ የሰማዩ አባታችሁም ይመግባቸዋል፤ እናንተ ከእነርሱ እጅግ አትበልጡምን?
Njòttu የማቴዎስ ወንጌል 6:26
11
የማቴዎስ ወንጌል 6:19-21
“ብልና ዝገት በሚያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በሚሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በምድር ላይ መዝገብ አትሰብስቡ፤ ነገር ግን ብልም ዝገትም በማያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በማይሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በሰማይ መዝገብ ሰብስቡ፤ መዝገብህ ባለበት ልብህ ደግሞ በዚያ ይሆናልና።
Njòttu የማቴዎስ ወንጌል 6:19-21
12
የማቴዎስ ወንጌል 6:24
“ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ማንም የለም፤ ወይም አንዱን ይጠላል ሁለተኛውንም ይወዳል፤ ወይም ወደ አንዱ ይጠጋል ሁለተኛውንም ይንቃል፤ ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም።
Njòttu የማቴዎስ ወንጌል 6:24
13
የማቴዎስ ወንጌል 6:30
እግዚአብሔር ግን ዛሬ ያለውን ነገም ወደ እቶን የሚጣለውን የሜዳን ሣር እንዲህ የሚያለብሰው ከሆነ፥ እናንተ እምነት የጎደላችሁ፥ እናንተንማ ይልቁን እንዴት?
Njòttu የማቴዎስ ወንጌል 6:30
14
የማቴዎስ ወንጌል 6:3-4-3-4
አንተ ግን ምጽዋት ስታደርግ ምጽዋትህ በስውር እንዲሆን ቀኝህ የምትሠራውን ግራህ አትወቅ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል።
Njòttu የማቴዎስ ወንጌል 6:3-4-3-4
15
የማቴዎስ ወንጌል 6:1
“ለሰዎች ትታዩ ዘንድ ምጽዋታችሁን በፊታቸው እንዳታደርጉ ተጠንቀቁ፤ ያለዚያ በሰማያት ባለው አባታችሁ ዘንድ ዋጋ የላችሁም።
Njòttu የማቴዎስ ወንጌል 6:1
16
የማቴዎስ ወንጌል 6:16-17-18
“ስትጦሙም፥ እንደ ግብዞች አትጠውልጉ፤ ለሰዎች እንደ ጦመኛ ሊታዩ ፊታቸውን ያጠፋሉና፤ እውነት እላችኋለሁ፤ ዋጋቸውን ተቀብለዋል። አንተ ግን ስትጦም፥ በስውር ላለው አባትህ እንጂ እንደ ጦመኛ ለሰዎች እንዳትታይ ራስህን ተቀባ፤ ፊትህንም ታጠብ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል።
Njòttu የማቴዎስ ወንጌል 6:16-17-18
Heim
Biblía
Áætlanir
Myndbönd