1
የዮሐንስ ወንጌል 15:5
መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)
አማ54
እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ያለ እኔ ምንም ልታደጉ አትችሉምና በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ፥ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል።
Lee anya n'etiti ihe abụọ
Nyochaa የዮሐንስ ወንጌል 15:5
2
የዮሐንስ ወንጌል 15:4
በእኔ ኑሩ እኔም በእንናተ። ቅርንጫፍ በወኑ ግንድ ባይኖር ከራሱ ፍሬ ሊያፈራ እንዳይቻለው፥ እንዲሁ እናንተ ደግሞ በእኔ ባትኖሩ አትችሉም።
Nyochaa የዮሐንስ ወንጌል 15:4
3
የዮሐንስ ወንጌል 15:7
በእኔ ብትኖሩ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ የምትወዱትን ሁሉ ለምኑ ይሆንላችሁማል።
Nyochaa የዮሐንስ ወንጌል 15:7
4
የዮሐንስ ወንጌል 15:16
እኔ መረጥኋችሁ እንጂ እናንተ አልመረጣችሁኝም፤ አብም በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ እንዲሰጣችሁ፥ ልትሄዱና ፍሬ ልታፈሩ ፍሬአችሁም ሊኖር ሾምኋችሁ።
Nyochaa የዮሐንስ ወንጌል 15:16
5
የዮሐንስ ወንጌል 15:13
ነፍሱን ስለ ወዳጆቹ ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም።
Nyochaa የዮሐንስ ወንጌል 15:13
6
የዮሐንስ ወንጌል 15:2
ፍሬ የማያፈራውን በእኔ ያለውን ቅርንጫፍ ሁሉ ያስወግደዋል፤ ፍሬ የሚያፈራውንም ሁሉ አብዝቶ እንዲያፈራ ያጠራዋል።
Nyochaa የዮሐንስ ወንጌል 15:2
7
የዮሐንስ ወንጌል 15:12
እኔ እንደ ወደድኋችሁ እርስ በርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ ትእዛዜ ይህች ናት።
Nyochaa የዮሐንስ ወንጌል 15:12
8
የዮሐንስ ወንጌል 15:8
ብዙ ፍሬ ብታፈሩና ደቀ መዛሙርቴ ብትሆኑ በዚህ አባቴ ይከብራል።
Nyochaa የዮሐንስ ወንጌል 15:8
9
የዮሐንስ ወንጌል 15:1
እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ፤ ገበሬውም አባቴ ነው።
Nyochaa የዮሐንስ ወንጌል 15:1
10
የዮሐንስ ወንጌል 15:6
በእኔ የማይኖር ቢሆን እንደ ቅርንጫፍ ወደ ውጭ ይጣላል ይደርቅማል፤ እነርሱንም ሰብስበው ወደ እሳት ይጥሉአቸዋል፥ ያቃጥሉአቸውማል።
Nyochaa የዮሐንስ ወንጌል 15:6
11
የዮሐንስ ወንጌል 15:11
ደስታዬም በእናንተ እንዲሆን ደስታችሁም እንዲፈጸም ይህን ነግሬአችኋለሁ።
Nyochaa የዮሐንስ ወንጌል 15:11
12
የዮሐንስ ወንጌል 15:10
እኔ የአባቴን ትእዛዝ እንደ ጠበቅሁ በፍቅሩም እንደምኖር፥ ትእዛዜን ብትጠብቁ በፍቅሬ ትኖራላችሁ።
Nyochaa የዮሐንስ ወንጌል 15:10
13
የዮሐንስ ወንጌል 15:17
እርስ በርሳችሁ እንድትዋደዱ ይህን አዛችኋለሁ።
Nyochaa የዮሐንስ ወንጌል 15:17
14
የዮሐንስ ወንጌል 15:19
ከዓለምስ ብትሆኑ ዓለም የራሱ የሆነውን ይወድ ነበር፤ ነገር ግን እኔ ከዓለም መረጥኋችሁ እንጂ ከዓለም ስለ አይደላችሁ ስለዚህ ዓለም ይጠላችኋል።
Nyochaa የዮሐንስ ወንጌል 15:19
Ebe Mmepe Nke Mbụ Nke Ngwá
Akwụkwọ Nsọ
Atụmatụ Ihe Ogụgụ Gasị
Vidiyo Gasị