1
ወደ ሮም ሰዎች 4:20-21
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
በእምነቱ ብርቱ ሆኖ ለእግዚአብሔር ክብር ሰጠ እንጂ እግዚአብሔር በሰጠው ተስፋ ባለማመን ከቶ አልተጠራጠረም። እግዚአብሔር የሰጠውንም ተስፋ የሚፈጽም መሆኑን በሙሉ ልብ ያምን ነበር።
Lee anya n'etiti ihe abụọ
Nyochaa ወደ ሮም ሰዎች 4:20-21
2
ወደ ሮም ሰዎች 4:17
ስለ አብርሃም፦ “የብዙ ሕዝብ አባት አድርጌሃለሁ” ተብሎ ተጽፎአል፤ ይህም ተስፋ ለአብርሃም የተሰጠው እርሱ የሞቱትን በሚያስነሣውና የሌለውን እንዲኖር በሚያደርገው አምላክ ስለ አመነ ነበር።
Nyochaa ወደ ሮም ሰዎች 4:17
3
ወደ ሮም ሰዎች 4:25
ይህ ጌታችን ኢየሱስም ስለ ኃጢአታችን ለሞት ተላልፎ የተሰጠውና እኛንም ለማጽደቅ ከሞት የተነሣው ነው።
Nyochaa ወደ ሮም ሰዎች 4:25
4
ወደ ሮም ሰዎች 4:18
አብርሃም ዘርህ እጅግ ይበዛል ተብሎ በተነገረው መሠረት የብዙ ሕዝብ አባት እንደሚሆን ያመነውና ተስፋ ያደረገው ምንም ተስፋ በማይጣልበት ነገር ነው።
Nyochaa ወደ ሮም ሰዎች 4:18
5
ወደ ሮም ሰዎች 4:16
ስለዚህ ተስፋው የተመሠረተው በእምነት ላይ ነበር፤ ይህም ተስፋ ለአብርሃም ዘሮች ሁሉ ከእግዚአብሔር በጸጋ የተሰጠ መሆኑ በዚህ ተረጋግጦአል። ይህም ሕግን ለሚከተሉት ሰዎች ብቻ ሳይሆን እንደ አብርሃም ላመኑ ሁሉ ነው፤ በዚህም መሠረት አብርሃም የሁላችንም አባት ነውና።
Nyochaa ወደ ሮም ሰዎች 4:16
6
ወደ ሮም ሰዎች 4:7-8
“በደላቸው ይቅር የተባለላቸውና ኃጢአታቸው የተደመሰሰላቸው ሰዎች የተባረኩ ናቸው! ጌታ ኃጢአቱን የማይቈጥርበት ሰው የተባረከ ነው!”
Nyochaa ወደ ሮም ሰዎች 4:7-8
7
ወደ ሮም ሰዎች 4:3
ቅዱስ መጽሐፍ “አብርሃም በእግዚአብሔር አመነ፤ እምነቱም ጽድቅ ሆኖ ተቈጠረለት” ይላል።
Nyochaa ወደ ሮም ሰዎች 4:3
Ebe Mmepe Nke Mbụ Nke Ngwá
Akwụkwọ Nsọ
Atụmatụ Ihe Ogụgụ Gasị
Vidiyo Gasị