1
ወደ ሮም ሰዎች 14:17-18
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
የእግዚአብሔር መንግሥት በመንፈስ ቅዱስ የሚገኝ ጽድቅ፥ ሰላምና ደስታ ነው እንጂ የመብልና የመጠጥ ጉዳይ አይደለም። በዚህ ሁኔታ ክርስቶስን የሚያገለግል ሰው እግዚአብሔርን ደስ ያሰኛል፤ በሰውም ዘንድ የተመሰገነ ነው።
Lee anya n'etiti ihe abụọ
Nyochaa ወደ ሮም ሰዎች 14:17-18
2
ወደ ሮም ሰዎች 14:8
ብንኖር ለጌታ እንኖራለን፤ ብንሞትም ለጌታ እንሞታለን፤ ስለዚህ ብንኖርም፥ ብንሞትም የጌታ ነን።
Nyochaa ወደ ሮም ሰዎች 14:8
3
ወደ ሮም ሰዎች 14:19
ስለዚህ ሰላም የሚገኝበትንና እርስ በርሳችን የምንታነጽበትን ነገር እንከተል።
Nyochaa ወደ ሮም ሰዎች 14:19
4
ወደ ሮም ሰዎች 14:13
ስለዚህ አንዳችን በአንዳችን ላይ አንፍረድ፤ ነገር ግን ማንም ሰው በወንድሙ መንገድ መሰናክል ወይም እንቅፋት ላለማኖር ይጠንቀቅ።
Nyochaa ወደ ሮም ሰዎች 14:13
5
ወደ ሮም ሰዎች 14:11-12
ምክንያቱም፦ “እኔ ሕያው ነኝ ይላል እግዚአብሔር፤ ሰው ሁሉ በጒልበቱ በእኔ ፊት ይንበረከካል፤ በአንደበቱም እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ይመሰክራል” ተብሎ ተጽፎአል። ስለዚህ እያንዳንዳችን ስለ ራሳችን ሥራ በእግዚአብሔር ፊት ቀርበን መልስ እንሰጣለን።
Nyochaa ወደ ሮም ሰዎች 14:11-12
6
ወደ ሮም ሰዎች 14:1
በእናንተ መካከል በእምነቱ ደካማ የሆነውን ሰው ተቀበሉት እንጂ በግል ሐሳቡ ላይ ክርክር አታንሡ።
Nyochaa ወደ ሮም ሰዎች 14:1
7
ወደ ሮም ሰዎች 14:4
ታዲያ፥ በሌላ ሰው አገልጋይ ላይ የምትፈርድ አንተ ማነህ? እርሱ ቢቆም ወይም ቢወድቅ የጌታው ጉዳይ ነው። እንዲያውም እግዚአብሔር ሊያቆመው ስለሚችል ጸንቶ ይቆማል።
Nyochaa ወደ ሮም ሰዎች 14:4
Ebe Mmepe Nke Mbụ Nke Ngwá
Akwụkwọ Nsọ
Atụmatụ Ihe Ogụgụ Gasị
Vidiyo Gasị