1
ኦሪት ዘጸአት 7:1
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ አለው፤ “እነሆ፥ እኔ አንተን ለፈርዖን እንደ አምላክ አደርግሃለሁ፤ ወንድምህም አሮን እንደ ነቢይ ሆኖ ስለ አንተ ይናገራል፤
Konpare
Eksplore ኦሪት ዘጸአት 7:1
2
ኦሪት ዘጸአት 7:3-4
ነገር ግን እኔ የንጉሡን ልብ አደነድናለሁ፤ ከዚህም የተነሣ እኔ የቱንም ያኽል ምልክቶችንና ተአምራትን በግብጽ ምድር ባደርግ፥ እናንተን አይሰማችሁም፤ ከዚያን በኋላ በግብጽ ላይ በታላቅ ፍርድ ብርቱ ቅጣት በማምጣት ሠራዊቴን፥ ሕዝቤን የእስራኤልን ልጆች ከምድረ ግብጽ አስወጣቸዋለሁ።
Eksplore ኦሪት ዘጸአት 7:3-4
3
ኦሪት ዘጸአት 7:5
በዚህ ዐይነት የኀይል ክንዴን በእነርሱ ላይ አንሥቼ እስራኤላውያንን ከአገራቸው በማወጣበት ጊዜ ግብጻውያን እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንኩ ያውቃሉ።”
Eksplore ኦሪት ዘጸአት 7:5
4
ኦሪት ዘጸአት 7:11-12
ከዚህም በኋላ ፈርዖን ጠቢባኑንና አስማተኞቹን ጠራ፤ እነርሱም በአስማታቸው እንደዚሁ አደረጉ። በትሮቻቸውን ወደ መሬት በጣሉአቸው ጊዜ ተለውጠው እባቦች ሆኑ፤ ነገር ግን የአሮን በትር የእነርሱን በትሮች ሁሉ ዋጠች።
Eksplore ኦሪት ዘጸአት 7:11-12
5
ኦሪት ዘጸአት 7:17
አሁን ግን በሚያደርገው ነገር የእግዚአብሔርን ማንነት በግድ ታውቃለህ፤ እነሆ፥ እኔ በዚህ በትር የአባይን ወንዝ ውሃ እመታለሁ፤ ውሃውም ወደ ደም ይለወጣል።
Eksplore ኦሪት ዘጸአት 7:17
6
ኦሪት ዘጸአት 7:9-10
“ፈርዖን ‘እስቲ ተአምራት በማድረግ ማንነታችሁን ግለጡልኝ’ ቢላችሁ ለአሮን ንገረውና በትሩን ወስዶ በንጉሡ ፊት ይጣለው፤ በዚያን ጊዜ በትሩ ተለውጦ እባብ ይሆናል።” ስለዚህ ሙሴና አሮን ወደ ፈርዖን ሄደው እግዚአብሔር እንዳዘዛቸው አደረጉ፤ አሮንም በትሩን በንጉሡና በመኳንንቱ ፊት በጣለው ጊዜ ተለውጦ እባብ ሆነ።
Eksplore ኦሪት ዘጸአት 7:9-10
Akèy
Bib
Plan yo
Videyo