1
የሐዋርያት ሥራ 2:38
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
ጴጥሮስም እንዲህ አላቸው፤ “ንስሓ ግቡ፤ ኃጢአታችሁም ይቅር እንዲባልላችሁ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የእግዚአብሔር ስጦታ የሆነውን መንፈስ ቅዱስንም ትቀበላላችሁ፤
Konpare
Eksplore የሐዋርያት ሥራ 2:38
2
የሐዋርያት ሥራ 2:42
እነርሱም የሐዋርያትን ትምህርት በመስማት፥ በኅብረት በመኖር፥ ማዕድን አብሮ በመብላትና በጸሎት ይተጉ ነበር።
Eksplore የሐዋርያት ሥራ 2:42
3
የሐዋርያት ሥራ 2:4
ሁሉም በመንፈስ ቅዱስ ተሞሉ፤ መንፈስ ቅዱስ እንዲናገሩ በሰጣቸው ችሎታ መጠን በሌሎች ቋንቋዎች መናገር ጀመሩ።
Eksplore የሐዋርያት ሥራ 2:4
4
የሐዋርያት ሥራ 2:2-4
በድንገት ብርቱ ዐውሎ ነፋስ የመሰለ ድምፅ ከሰማይ መጣ፤ የነበሩበትንም ቤት ሞላው። የእሳት ነበልባሎች የሚመስሉ ልሳኖች ታዩአቸው፤ ተከፋፍለውም በእያንዳንዳቸው ላይ ዐረፉባቸው። ሁሉም በመንፈስ ቅዱስ ተሞሉ፤ መንፈስ ቅዱስ እንዲናገሩ በሰጣቸው ችሎታ መጠን በሌሎች ቋንቋዎች መናገር ጀመሩ።
Eksplore የሐዋርያት ሥራ 2:2-4
5
የሐዋርያት ሥራ 2:46-47
በየቀኑ በቤተ መቅደስ በአንድነት ይሰበሰቡ ነበር፤ በቤታቸውም እንጀራ እየቈረሱ በደስታና በጥሩ ልብ ይመገቡ ነበር፤ ጌታንም ያመሰግኑ ነበር፤ ሰውም ሁሉ ያከብራቸው ነበር፤ እግዚአብሔርም የሚድኑትን ሰዎች በየቀኑ ወደ ማኅበራቸው ይጨምር ነበር።
Eksplore የሐዋርያት ሥራ 2:46-47
6
የሐዋርያት ሥራ 2:17
‘እግዚአብሔር በመጨረሻው ቀን እንዲህ ይሆናል ይላል፤ መንፈሴን በሰው ሁሉ ላይ አፈሳለሁ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁ ትንቢት ይናገራሉ፤ ጐልማሶቻችሁም ራእይ ያያሉ፤ ሽማግሌዎቻችሁም ሕልም ያልማሉ።
Eksplore የሐዋርያት ሥራ 2:17
7
የሐዋርያት ሥራ 2:44-45
አማኞች ሁሉ በአንድነት አብረው ይኖሩ ነበር፤ ያላቸውም ነገር ሁሉ የጋራ ነበር። ዕርሻቸውንና ሀብታቸውን እየሸጡ ገንዘቡን ለእያንዳንዱ እንደሚያስፈልገው ያከፋፍሉ ነበር።
Eksplore የሐዋርያት ሥራ 2:44-45
8
የሐዋርያት ሥራ 2:21
የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል።’
Eksplore የሐዋርያት ሥራ 2:21
9
የሐዋርያት ሥራ 2:20
ታላቁና አስገራሚው የጌታ ቀን ከመምጣቱ በፊት፥ ፀሐይ ይጨልማል፤ ጨረቃም ደም ትመስላለች።
Eksplore የሐዋርያት ሥራ 2:20
Akèy
Bib
Plan yo
Videyo