1
የዮሐንስ ወንጌል 14:27
መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)
አማ54
ሰላምን እተውላችኋለሁ፥ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም። ልባችሁ አይታወክ አይፍራም።
השווה
חקרו የዮሐንስ ወንጌል 14:27
2
የዮሐንስ ወንጌል 14:6
ኢየሱስም፦ “እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።
חקרו የዮሐንስ ወንጌል 14:6
3
የዮሐንስ ወንጌል 14:1
“ልባችሁ አይታወክ፤ በእግዚአብሔር እመኑ፥ በእኔም ደግሞ እመኑ።
חקרו የዮሐንስ ወንጌል 14:1
4
የዮሐንስ ወንጌል 14:26
አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል።
חקרו የዮሐንስ ወንጌል 14:26
5
የዮሐንስ ወንጌል 14:21
ትእዛዜ በእርሱ ዘንድ ያለችው የሚጠብቃትንም የሚወደኝ እርሱ ነው፤ የሚወደኝንም አባቴ ይወደዋል እኔም እወደዋለሁ ራሴንም እገልጥለታለሁ።”
חקרו የዮሐንስ ወንጌል 14:21
6
የዮሐንስ ወንጌል 14:15-16-17
“ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ። እኔም አብን እለምናለሁ በዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤ እርሱም ዓለም የማያየውና የማያውቀው ስለ ሆነ ሊቀበለው የማይቻለው የእውነት መንፈስ ነው፤ ነገር ግን ከእናንተ ዘንድ ስለሚኖር በውሥጣችሁም ስለሚሆን እናንተ ታውቃላችሁ።
חקרו የዮሐንስ ወንጌል 14:15-16-17
7
የዮሐንስ ወንጌል 14:13-14
እኔ ወደ አብ እሄዳለሁና አብም ስለ ወልድ እንዲከብር በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አደርገዋለሁ። ማናቸውንም ነገር በስሜ ብትለምኑ እኔ አደርገዋለሁ።
חקרו የዮሐንስ ወንጌል 14:13-14
8
የዮሐንስ ወንጌል 14:15-16
“ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ። እኔም አብን እለምናለሁ በዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤
חקרו የዮሐንስ ወንጌል 14:15-16
9
የዮሐንስ ወንጌል 14:2
በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፤ እንዲህስ ባይሆን ባልኋችሁ ነበር፤ ስፍራ አዘጋጅላችሁ ዘንድ እሄዳለሁና
חקרו የዮሐንስ ወንጌል 14:2
10
የዮሐንስ ወንጌል 14:3
ሄጄም ስፍራ ባዘጋጅላችሁ፥ እኔ ባለሁበት እናንተ ደግሞ እንድትሆኑ ሁለተኛ እመጣለሁ ወደ እኔም እወስዳችኋለሁ።
חקרו የዮሐንስ ወንጌል 14:3
11
የዮሐንስ ወንጌል 14:5
ቶማስም፦ “ጌታ ሆይ፥ ወደምትሄድበት አናውቅም፤ እንዴትስ መንገዱን እናውቃለን?” አለው።
חקרו የዮሐንስ ወንጌል 14:5
בית
כתבי הקודש
תכניות
קטעי וידאו