1
ወደ ሮሜ ሰዎች 3:23-24
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
አማ2000
በዚህም ልዩነት የለም፤ ሁሉም ፈጽመው በድለዋልና፤ እግዚአብሔርን ማክበርንም ትተዋልና። ጽድቅ ግን በኢየሱስ ክርስቶስም ቤዛነት ያለ ዋጋ በእርሱ ቸርነት ሆነ።
השווה
חקרו ወደ ሮሜ ሰዎች 3:23-24
2
ወደ ሮሜ ሰዎች 3:22
የሚያምኑበት ሁሉ ኢየሱስ ክርስቶስን በማመን በእግዚአብሔር ዘንድ ይጸድቃሉ።
חקרו ወደ ሮሜ ሰዎች 3:22
3
ወደ ሮሜ ሰዎች 3:25-26
እርሱንም እግዚአብሔር በእምነት የሚገኝ፥ በደሙም የሆነ ማስተስረያ አድርጎ አቆመው፤ ይህም ከጥንት ጀምሮ በበደሉት ላይ ጽድቁን ይገልጥ ዘንድ ነው። እግዚአብሔር ታጋሽ በመሆኑ፥ እሺ በማለቱም እርሱ ጻድቅ እንደ ሆነ፥ በኢየሱስ ክርስቶስም የሚያምኑትን እንደሚያጸድቃቸው ዛሬ ያውቁ ዘንድ ነው።
חקרו ወደ ሮሜ ሰዎች 3:25-26
4
ወደ ሮሜ ሰዎች 3:20
ከኦሪት የተነሣ ኀጢአት ስለ ታወቀች ሰው ሁሉ የኦሪትን ሥርዐት በመፈጸም በእግዚአብሔር ፊት አይጸድቅም።
חקרו ወደ ሮሜ ሰዎች 3:20
5
ወደ ሮሜ ሰዎች 3:10-12
መጽሐፍ እንዲህ እንዳለ “አንድ ስንኳ ጻድቅ የለም። አስተዋይም የለም፤ እግዚአብሔርንም የሚሻው የለም። ሁሉም ተባብሮ በደለ፤ በጎ ሥራንም የሚሠራ የለም፤ አንድ ስንኳ ቢሆን የለም።
חקרו ወደ ሮሜ ሰዎች 3:10-12
6
ወደ ሮሜ ሰዎች 3:28
ሰው የኦሪትን ሥራ ሳይሠራ በእምነት እንዲጸድቅ እናውቃለንና።
חקרו ወደ ሮሜ ሰዎች 3:28
7
ወደ ሮሜ ሰዎች 3:4
መጽሐፍ፥ “በነገርህ ትጸድቅ ዘንድ፥ በፍርድህም ታሸንፍ ዘንድ” ብሎ እንደ ተናገረ እግዚአብሔር እውነተና ነውና፥ ሰውም ሁሉ ሐሰተና ነውና።
חקרו ወደ ሮሜ ሰዎች 3:4
בית
כתבי הקודש
תכניות
קטעי וידאו