1
ወደ ገላትያ ሰዎች 6:9
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መቅካእኤ
መልካምን ሥራ ለመሥራት አንታክት፥ ካልዛልን ወቅቱ በደረሰ ጊዜ እናጭዳለንና።
השווה
חקרו ወደ ገላትያ ሰዎች 6:9
2
ወደ ገላትያ ሰዎች 6:10
ስለዚህ ጊዜ ሳለን ለሰው ሁሉ፥ በተለይም ለእምነት ቤተሰቦች መልካም እናድርግ።
חקרו ወደ ገላትያ ሰዎች 6:10
3
ወደ ገላትያ ሰዎች 6:2
የእርስ በርሳችሁን ሸክም ተሸከሙ፥ በዚህም የክርስቶስን ሕግ ትፈጽማላችሁ።
חקרו ወደ ገላትያ ሰዎች 6:2
4
ወደ ገላትያ ሰዎች 6:7
አትሳቱ፤ እግዚአብሔር አይዘበትበትም፤ ሰው የዘራውን ያንኑ ያጭዳልና።
חקרו ወደ ገላትያ ሰዎች 6:7
5
ወደ ገላትያ ሰዎች 6:8
ምክንያቱም ወደ ገዛ ሥጋው የሚዘራ ከሥጋ ጥፋትን ያጭዳል፥ በመንፈስ የሚዘራ ግን ከመንፈስ የዘለዓለምን ሕይወት ያጭዳል።
חקרו ወደ ገላትያ ሰዎች 6:8
6
ወደ ገላትያ ሰዎች 6:1
ወንድሞች ሆይ! ሰው ማንኛውንም ኃጢአት አድርጎ ቢገኝ፥ መንፈሳውያን የሆናችሁ እናንተ እንደዚህ ዓይነቱን ሰው በየውሃት መንፈስ አቅኑት፤ አንተም እንዳትፈተን ራስህን ጠብቅ።
חקרו ወደ ገላትያ ሰዎች 6:1
7
ወደ ገላትያ ሰዎች 6:3-5
አንድ ሰው ምንም ሳይሆን አንድ ነገር የሆነ ቢመስለው ራሱን ያታልላልና። እያንዳንዱ የገዛ ሥራውን ይፈትን፤ ከዚያም በኋላ ስለ ራሱ ብቻ የሚመካበትን ያገኛል፥ ስለ ሌላው ግን አይደለም። እያንዳንዱ የገዛ ራሱን ሸክም ይሸከማልና።
חקרו ወደ ገላትያ ሰዎች 6:3-5
בית
כתבי הקודש
תכניות
קטעי וידאו