1
ኦሪት ዘጸአት 20:2-3
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
“የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! በባርነት ከምትኖርባት ከግብጽ ምድር ያወጣሁህ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ነኝ፤ “ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ አታምልክ፤
השווה
חקרו ኦሪት ዘጸአት 20:2-3
2
ኦሪት ዘጸአት 20:4-5
“በሰማይም ሆነ በምድር ወይም ከምድር በታች ባለው ውሃ ውስጥ ከሚኖሩት ነገሮች የማንኛውንም ዐይነት ምስል ጣዖት አድርገህ አትሥራ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ እጅግ ቀናተኛ ስለ ሆንኩ ተቀርጾ የተሠራውን ማንኛውም ጣዖት አታምልክ፤ አትስገድለትም፤ እኔ የሚጠሉኝን ሁሉ እቀጣለሁ፤ ዘራቸውንም ሁሉ እስከ ሦስትና አራት ትውልድ ድረስ እበቀላለሁ።
חקרו ኦሪት ዘጸአት 20:4-5
3
ኦሪት ዘጸአት 20:12
“አባትህንና እናትህን አክብር፤ ይህን ብታደርግ እኔ በምሰጥህ ምድር የረዥም ዘመን ዕድሜ ይኖርሃል።
חקרו ኦሪት ዘጸአት 20:12
4
ኦሪት ዘጸአት 20:8
“የሰንበትን ቀን አክብር፤ ቀድሰውም፤
חקרו ኦሪት ዘጸአት 20:8
5
ኦሪት ዘጸአት 20:7
“የአምላክህን የእግዚአብሔርን ስም በከንቱ አታንሣ፤ እግዚአብሔር ስሙን በከንቱ የሚያነሣውን ሁሉ ሳይቀጣው አያልፍም።
חקרו ኦሪት ዘጸአት 20:7
6
ኦሪት ዘጸአት 20:9-10
ሥራህን ሁሉ የምታከናውንባቸው ስድስት ቀኖች አሉልህ፤ ሰባተኛው ቀን ግን ለአምላክህ ለእግዚአብሔር የዕረፍት ቀን ነው፤ በዚያን ቀን ማንም ሰው ሥራ አይሥራ፤ አንተም ሆንክ ልጆችህ፥ አገልጋዮችህም ሆኑ እንስሶችህ፥ በአገርህ ውስጥ የሚኖሩ መጻተኞችም ቢሆኑ ምንም ሥራ አትሥሩበት።
חקרו ኦሪት ዘጸአት 20:9-10
7
ኦሪት ዘጸአት 20:17
“የሌላውን ሰው ቤት አትመኝ፤ ሚስቱን፥ አገልጋዮቹን፥ ከብቱን፥ አህዮቹንም ሆነ ማናቸውንም ንብረቱን ሁሉ አትመኝ።”
חקרו ኦሪት ዘጸአት 20:17
8
ኦሪት ዘጸአት 20:16
“በማንም ሰው ላይ በሐሰት አትመስክር፤
חקרו ኦሪት ዘጸአት 20:16
9
ኦሪት ዘጸአት 20:14
“አታመንዝር፤
חקרו ኦሪት ዘጸአት 20:14
10
ኦሪት ዘጸአት 20:13
“አትግደል፤
חקרו ኦሪት ዘጸአት 20:13
11
ኦሪት ዘጸአት 20:15
“አትስረቅ፤
חקרו ኦሪት ዘጸአት 20:15
בית
כתבי הקודש
תכניות
קטעי וידאו