1
የማርቆስ ወንጌል 2:17
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መቅካእኤ
ኢየሱስም ሰምቶ “ሕመምተኞች እንጂ ጤነኞች ባለ መድኃኒት አያስፈልጋቸውም፤ ኀጢአተኞችን እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁም፤” አላቸው።
Compare
የማርቆስ ወንጌል 2:17 ખોજ કરો
2
የማርቆስ ወንጌል 2:5
ኢየሱስም እምነታቸውን አይቶ ሽባውን “አንተ ልጅ! ኃጢአትህ ተሰርዮልሃል፤” አለው።
የማርቆስ ወንጌል 2:5 ખોજ કરો
3
የማርቆስ ወንጌል 2:27
ደግሞ “ሰንበት ስለ ሰው ተፈጥሯል እንጂ ሰው ስለ ሰንበት አልተፈጠረም፤
የማርቆስ ወንጌል 2:27 ખોજ કરો
4
የማርቆስ ወንጌል 2:4
ከሕዝቡ ብዛት የተነሣ ወደ እርሱ ማቅረብ ስላልቻሉ፥ እርሱ ያለበትን የቤቱን ጣራ አነሡ፤ ነድለውም ሽባው የተኛበትን አልጋ አወረዱ።
የማርቆስ ወንጌል 2:4 ખોજ કરો
5
የማርቆስ ወንጌል 2:10-11
ነገር ግን ለሰው ልጅ በምድር ላይ ኃጢአትን ሊያስተሰርይ ሥልጣን እንዳለው እንድታውቁ፤” ብሎ ሽባውን፦ “አንተን እልሃለሁ፥ ተነሣ፤ አልጋህን ተሸከምና ወደ ቤትህ ሂድ፤” አለው።
የማርቆስ ወንጌል 2:10-11 ખોજ કરો
6
የማርቆስ ወንጌል 2:9
ሽባውን ‘ኃጢአትህ ተሰርዮልሃል፤’ ከማለትና ‘ተነሣ አልጋህንም ተሸከምና ሂድ፤’ ከማለት የቱ ይቀላል?
የማርቆስ ወንጌል 2:9 ખોજ કરો
7
የማርቆስ ወንጌል 2:12
እርሱም ተነሥቶ ሁሉም እያዩት ወዲያው አልጋውን ተሸክሞ ሄደ፤ ስለዚህም ሰዎቹ ሁሉ ተደንቀው “እንዲህ ያለ ነገር ፈጽሞ አይተን አናውቅም፤” እያሉ እግዚአብሔርን አከበሩ።
የማርቆስ ወንጌል 2:12 ખોજ કરો
હોમ
બાઇબલ
યોજનાઓ
વિડિઓઝ