1
ወደ ሮም ሰዎች 12:2
መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)
አማ54
የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።
Compare
Avasta ወደ ሮም ሰዎች 12:2
2
ወደ ሮም ሰዎች 12:1
እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ሰውነታችሁን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና ሕያው ቅዱስም መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፥ እርሱም ለአእምሮ የሚመች አገልግሎታችሁ ነው።
Avasta ወደ ሮም ሰዎች 12:1
3
ወደ ሮም ሰዎች 12:12
በተስፋ ደስ ይበላችሁ፤ በመከራ ታገሡ፤ በጸሎት ጽኑ፤
Avasta ወደ ሮም ሰዎች 12:12
4
ወደ ሮም ሰዎች 12:21
ክፉውን በመልካም አሸንፍ እንጂ በክፉ አትሸነፍ።
Avasta ወደ ሮም ሰዎች 12:21
5
ወደ ሮም ሰዎች 12:10
በወንድማማች መዋደድ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ፤ እርስ በርሳችሁ ተከባበሩ፤
Avasta ወደ ሮም ሰዎች 12:10
6
ወደ ሮም ሰዎች 12:9
ፍቅራችሁ ያለ ግብዝነት ይሁን። ክፉውን ነገር ተጸየፉት፤ ከበጎ ነገር ጋር ተባበሩ፤
Avasta ወደ ሮም ሰዎች 12:9
7
ወደ ሮም ሰዎች 12:18
ቢቻላችሁስ በእናንተ በኩል ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ።
Avasta ወደ ሮም ሰዎች 12:18
8
ወደ ሮም ሰዎች 12:19
ተወዳጆች ሆይ፥ ራሳችሁ አትበቀሉ፥ ለቍጣው ፈንታ ስጡ እንጂ፤ በቀል የእኔ ነው፥ እኔ ብድራቱን እመልሳለሁ ይላል ጌታ ተብሎ ተጽፎአልና።
Avasta ወደ ሮም ሰዎች 12:19
9
ወደ ሮም ሰዎች 12:11
ለሥራ ከመትጋት አትለግሙ፤ በመንፈስ የምትቃጠሉ ሁኑ፤ ለጌታ ተገዙ፤
Avasta ወደ ሮም ሰዎች 12:11
10
ወደ ሮም ሰዎች 12:3
እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ የእምነትን መጠን እንዳካፈለው፥ እንደ ባለ አእምሮ እንዲያስብ እንጂ ማሰብ ከሚገባው አልፎ በትዕቢት እንዳያስብ በመካከላችሁ ላለው ለእያንዳንዱ በተሰጠኝ ጸጋ እናገራለሁ።
Avasta ወደ ሮም ሰዎች 12:3
11
ወደ ሮም ሰዎች 12:17
ለማንም ስለ ክፉ ፈንታ ክፉን አትመልሱ፤ በሰው ሁሉ ፊት መልካም የሆነውን አስቡ።
Avasta ወደ ሮም ሰዎች 12:17
12
ወደ ሮም ሰዎች 12:16
እርስ በርሳችሁ በአንድ አሳብ ተስማሙ፤ የትዕቢትን ነገር አታስቡ፥ ነገር ግን የትሕትናን ነገር ለመሥራት ትጉ። ልባሞች የሆናችሁ አይምሰላችሁ።
Avasta ወደ ሮም ሰዎች 12:16
13
ወደ ሮም ሰዎች 12:20
ጠላትህ ግን ቢራብ አብላው፤ ቢጠማ አጠጣው፤ ይህን በማድረግህ በራሱ ላይ የእሳት ፍም ትከምራለህና።
Avasta ወደ ሮም ሰዎች 12:20
14
ወደ ሮም ሰዎች 12:14-15
የሚያሳድዱአችሁን መርቁ፥ መርቁ እንጂ አትርገሙ። ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችሁ፥ ከሚያለቅሱም ጋር አልቅሱ።
Avasta ወደ ሮም ሰዎች 12:14-15
15
ወደ ሮም ሰዎች 12:13
ቅዱሳንን በሚያስፈልጋቸው እርዱ፤ እንግዶችን ለመቀበል ትጉ።
Avasta ወደ ሮም ሰዎች 12:13
16
ወደ ሮም ሰዎች 12:4-5
በአንድ አካል ብዙ ብልቶች እንዳሉን፥ የብልቶቹም ሁሉ ሥራ አንድ እንዳይደለ፥ እንዲሁ ብዙዎች ስንሆን በክርስቶስ አንድ አካል ነን፥ እርስ በርሳችንም እያንዳንዳችን የሌላው ብልቶች ነን።
Avasta ወደ ሮም ሰዎች 12:4-5
Home
Bible
Plans
Videod