1
ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4:32
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መቅካእኤ
እርስ በርሳችሁም ቸሮችና ርኅሩኆች ሁኑ፤ እግዚአብሔር በክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ ይቅር ተባባሉ።
Compare
Avasta ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4:32
2
ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4:2
በትሕትናና በየዋህነት ሁሉ፥ በትዕግሥትም እርስ በርሳችሁ በፍቅር ታገሡ፤
Avasta ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4:2
3
ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4:29
እንደ አስፈላጊነቱ፥ ለሚሰሙት ጸጋን እንዲሰጥ፥ ለማነጽ የሚጠቅም በጎ ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ።
Avasta ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4:29
4
ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4:31
መራርነትና ንዴት ቁጣም፥ ጩኸትና ስድብን ሁሉ፥ ከክፋት ሁሉ ጋር ከእናንተ ዘንድ ይወገድ።
Avasta ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4:31
5
ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4:26-27
ተቆጡ፥ ኃጢአትን ግን አታድርጉ፤ በቁጣችሁ ላይ ፀሐይ አይግባ፤ ለዲያብሎስም ስፍራ አትስጡት።
Avasta ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4:26-27
6
ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4:22-24
ስለ ቀድሞ አኗኗሯችሁም፥ በሚያታልል ምኞቱ የጎደፈውንና የተበላሸውን፥ አሮጌ ሰው አውልቃችሁ እንድትጥሉ ተምራችኋል፤ በአእምሮአችሁም መንፈስ ታደሱ፤ ለእውነትም በሚሆኑ ጽድቅና ቅድስና እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠረውን አዲሱን ሰው ልበሱ።
Avasta ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4:22-24
7
ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4:3
በሰላም ማሰሪያ የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ።
Avasta ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4:3
8
ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4:11-13
አንዳንዶቹ ሐዋርያት፥ ሌሎቹም ነቢያት፥ ሌሎቹም ወንጌልን ሰባኪዎች፥ ሌሎቹም እረኞችና አስተማሪዎች እንዲሆኑ የሰጠ እርሱ ነው፤ ይህም የክርስቶስ አካል ለመገንባት፥ ቅዱሳንን ለአገልግሎት ሥራ ለማዘጋጀት ነው፤ ይህም ሁላችን የእግዚአብሔርን ልጅ በማመንና በማወቅ ወደሚገኝ አንድነት፥ ሙሉ ሰውም ወደ መሆን፥ የክርስቶስም ሙላቱ ወደሚሆን ወደ ፍጽምናው እስክንደርስ ድረስ ነው።
Avasta ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4:11-13
9
ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4:14-15
ከእንግዲህ እንደ ስሕተት ሽንገላ ባለ ተንኮል፥ በሰዎችም ማታለል ምክንያት፥ በነፈሰው የትምህርት ነፋስ ሁሉ እየተፍገመገምን፥ ወዲያና ወዲህም እየተንሳፈፍን፥ ሕፃናት መሆን አይገባንም። ነገር ግን እውነትን በፍቅር እየተናገርን፥ በነገር ሁሉ ራስ ወደሚሆን ወደ እርሱ ወደ ክርስቶስ እንደግ፤
Avasta ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4:14-15
Home
Bible
Plans
Videod