Λογότυπο YouVersion
Εικονίδιο αναζήτησης

ኦሪት ዘሌዋውያን 12

12
ሴቶች ልጅ ከወለዱ በኋላ የሚደረግ የመንጻት ሥርዓት
1ጌታም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ 2#ዘሌ. 15፥19።ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ተናገር፦ ሴት ፀንሳ ወንድ ልጅም ብትወልድ፥ ሰባት ቀን ያኽል የረከሰች ትሆናለች፤ እንደ ወር አበባዋም ጊዜያት ትረክሳለች። 3#ዘፍ. 17፥12፤ ዮሐ. 7፥22።በስምንተኛውም ቀን ልጁ ከሥጋው ሸለፈት ይገረዝ። 4ከደምዋም እስክትነጻ ሠላሳ ሦስት ቀን ትቀመጥ፤የመንጻትዋ ቀንም እስኪፈጸም ድረስ የተቀደሰን ነገር ሁሉ አትንካ፥ ወደ መቅደስም አትግባ። 5ነገር ግን ሴት ልጅ ብትወልድ እንደ ወር አበባዋ ጊዜያት ሁለት ሳምንት ያኽል የረከሰች ትሆናለች፤ ከደምዋም እስክትነጻ ድረስ ስልሳ ስድስት ቀን ትቀመጥ።
6 # ሉቃ. 2፥22-24። “የመንጻትዋ ወራትም በተፈጸመ ጊዜ፥ ለወንድ ልጅ ወይም ለሴት ልጅ፥ የአንድ ዓመት ጠቦት ለሚቃጠል መሥዋዕት፥ የርግብም ግልገል ወይም ዋኖስ ለኃጢአት መሥዋዕት ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ወደ ካህኑ ታምጣ። 7እርሱም በጌታ ፊት ያቀርበዋል ያስተሰርይላታልም፤ ከሚፈስሰውም ደምዋ ትነጻለች። ወንድ ወይም ሴት ለምትወልድ ሴት ሕጉ ይህ ነው። 8#ዘሌ. 14፥21-22።ጠቦት ለማቅረብ በቂ ገንዘብ ባታገኝ ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የርግብ ግልገሎች ትውሰድ፥ አንዱን ለሚቃጠል መሥዋዕት ሌላውንም ለኃጢአት መሥዋዕት ታድርገው፤ ካህኑም ያስተሰርይላታል፥ እርሷም ትነጻለች።”#ዘሌ. 1፥14፤ ሉቃ. 2፥24።

Επιλέχθηκαν προς το παρόν:

ኦሪት ዘሌዋውያን 12: መቅካእኤ

Επισημάνσεις

Κοινοποίηση

Αντιγραφή

None

Θέλετε να αποθηκεύονται οι επισημάνσεις σας σε όλες τις συσκευές σας; Εγγραφείτε ή συνδεθείτε