1
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:28
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መቅካእኤ
እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ ዓላማውም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን።
Σύγκριση
Διαβάστε ወደ ሮሜ ሰዎች 8:28
2
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:38-39
ይህንን ተረድቼአለሁ፤ ሞትም ቢሆን፥ ሕይወትም ቢሆን፥ መላእክትም ቢሆኑ፥ ገዢዎችም ቢሆኑ፥ ያለውም ቢሆን፥ የሚመጣውም ቢሆን፥ ኃይላትም ቢሆኑ፥ ከፍታም ቢሆን፥ ጥልቀትም ቢሆን፥ ሌላ ፍጥረትም ቢሆን በጌታችን በክርስቶስ ኢየሱስ ካለው ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን አይችልም።
Διαβάστε ወደ ሮሜ ሰዎች 8:38-39
3
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:26
እንዲሁም ደግሞ መንፈስ በድካማችን ይረዳናል፤ እንዴት መጸለይ እንደሚገባን አናውቅምና፥ ነገር ግን መንፈስ ራሱ በቃላት ሊገለጥ በማይችል መቃተት ለእኛ ያማልድልናል፤
Διαβάστε ወደ ሮሜ ሰዎች 8:26
4
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:31
እንግዲህ ስለ እነዚህ ነገሮች ምን እንላለን? እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል?
Διαβάστε ወደ ሮሜ ሰዎች 8:31
5
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:1
ስለዚህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኩነኔ የለባቸውም።
Διαβάστε ወደ ሮሜ ሰዎች 8:1
6
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:6
ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነውና፥ ስለ መንፈስ ማሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው።
Διαβάστε ወደ ሮሜ ሰዎች 8:6
7
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:37
በእነዚህ ነገሮች ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን።
Διαβάστε ወደ ሮሜ ሰዎች 8:37
8
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:18
የአሁኑ ዘመን ሥቃይ ወደ ፊት ለእኛ ከሚገለጥልን ክብር ጋር ሲነጻጸር ምንም ዋጋ እንደሌለው እቆጥረዋለሁ።
Διαβάστε ወደ ሮሜ ሰዎች 8:18
9
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:35
ከክርስቶስ ፍቅር የሚለየን ማን ነው? መከራ ወይስ ሥቃይ፥ ወይስ ስደት፥ ወይስ ረሃብ፥ ወይስ ራቁትነት፥ ወይስ አደጋ፥ ወይስ ሰይፍ?
Διαβάστε ወደ ሮሜ ሰዎች 8:35
10
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:27
ልቦችንም የሚመረምረው እርሱ የመንፈስ ሐሳብ ምን እንደሆነ ያውቃል፥ ምክንያቱም መንፈስ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ስለ ቅዱሳን ያማልዳልና።
Διαβάστε ወደ ሮሜ ሰዎች 8:27
11
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:14
በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ፥ እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸውና።
Διαβάστε ወደ ሮሜ ሰዎች 8:14
12
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:5
እንደ ሥጋ የሚኖሩ አእምሮአቸው የሥጋን ነገር እንዲያስብ ያደርጋሉና፥ እንደ መንፈስ የሚኖሩ ግን አእምሮአቸው የመንፈስን ነገር እንዲያስብ ያደርጋሉ።
Διαβάστε ወደ ሮሜ ሰዎች 8:5
13
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:32
ለገዛ ልጁ ያልራራለት ነገር ግን ስለ ሁላችን አሳልፎ የሰጠው እርሱ፥ ከእርሱ ጋር ደግሞ ሁሉን ነገር እንዲያው እንዴት አይሰጠንም?
Διαβάστε ወደ ሮሜ ሰዎች 8:32
14
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:16-17
የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን መንፈሱ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክርልናል። ልጆች ከሆንን ወራሾች ደግሞ ነን፤ ከእርሱ ጋር የክብሩ ተካፋዮች እንድንሆን ከእርሱ ጋር መከራ ብንቀበል የእግዚአብሔር ወራሾችና ከክርስቶስም ጋር አብረን ወራሾች ነን።
Διαβάστε ወደ ሮሜ ሰዎች 8:16-17
15
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:7
ስለ ሥጋ ማሰብ የእግዚአብሔር ጠላት መሆን ነው፤ ለእግዚአብሔር ሕግ አይገዛምና፥ መገዛትም አይችልም፥
Διαβάστε ወደ ሮሜ ሰዎች 8:7
16
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:19
ፍጥረት ሁሉ የእግዚአብሔርን ልጆች መገለጥ በታላቅ ናፍቆት ይጠባበቃልና።
Διαβάστε ወደ ሮሜ ሰዎች 8:19
17
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:22
እስከ አሁን ድረስ ፍጥረት ሁሉ አብሮ በመቃተትና በምጥ ሥቃይ እንደሚኖር እናውቃለንና።
Διαβάστε ወደ ሮሜ ሰዎች 8:22
Αρχική
Αγία Γραφή
Σχέδια
Βίντεο