1
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:2
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መቅካእኤ
መልካም፥ ደስ የሚያሰኝና ፍጹም የሆነውን የእግዚአብሔር ፈቃድ ምን እንደሆነ ለማወቅ በአእምሮአችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።
Σύγκριση
Διαβάστε ወደ ሮሜ ሰዎች 12:2
2
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:1
እንግዲህ ወንድሞች ሆይ! ሰውነታችሁን ሕያው መሥዋዕት፥ ቅዱስና እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ አድርጋችሁ እንድታቀርቡ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፤ ይህም መንፈሳዊ አገልግሎታችሁ ነው።
Διαβάστε ወደ ሮሜ ሰዎች 12:1
3
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:12
በተስፋ ደስ ይበላችሁ፤ በመከራ ታገሡ፤ በጸሎት ጽኑ፤
Διαβάστε ወደ ሮሜ ሰዎች 12:12
4
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:21
ክፉውን በመልካም አሸንፍ እንጂ በክፉ አትሸነፍ።
Διαβάστε ወደ ሮሜ ሰዎች 12:21
5
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:10
እርስ በእርሳችሁ በወንድማማችነት መዋደድ አጥብቃችሁ ተዋደዱ፤ እርስ በርሳችሁ ይበልጥ ተከባበሩ፤
Διαβάστε ወደ ሮሜ ሰዎች 12:10
6
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:9
ፍቅር እውነተኛ ይሁን፤ ክፉውን ነገር ተጸየፉ፥ መልካም የሆነው ነገር አጥብቃችሁ ያዙ፤
Διαβάστε ወደ ሮሜ ሰዎች 12:9
7
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:18
ቢቻላችሁ በእናንተ በኩል ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ።
Διαβάστε ወደ ሮሜ ሰዎች 12:18
8
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:19
“በቀል የእኔ ነው፤ እኔ ብድራቱን እመልሳለሁ፤ ይላል ጌታ” ተብሎ ተጽፎአልና፥ ተወዳጆች ሆይ! ራሳችሁ አትበቀሉ፤ ለቁጣው ቦታ ስጡ እንጂ።
Διαβάστε ወደ ሮሜ ሰዎች 12:19
9
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:11
ለሥራ ከመትጋት አትለግሙ፤ በመንፈስ የምትቃጠሉ ሁኑ፤ ጌታን አገልግሉ፤
Διαβάστε ወደ ሮሜ ሰዎች 12:11
10
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:3
እግዚአብሔር ለእያንዳንዳችሁ እንደሰጣችሁ እምነት መጠን፥ በረጋ አእምሮ አስቡ እንጂ ማሰብ ከሚገባችሁ በላይ ራሳችሁን ከፍ አድርጋችሁ እንዳታስቡ በተሰጠኝ ጸጋ በመካከላችሁ ላለው ለእያንዳንዱ እናገራለሁና።
Διαβάστε ወደ ሮሜ ሰዎች 12:3
11
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:17
ለማንም በክፉ ፈንታ ክፉን አትመልሱ፤ በሰው ሁሉ ፊት መልካም የሆነውን ነገር አስቡ።
Διαβάστε ወደ ሮሜ ሰዎች 12:17
12
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:16
እርስ በርሳችሁ በአንድ ነገር ተስማሙ፤ የትዕቢትን ነገር አታስቡ፤ ነገር ግን የተናቁትን ቅረቡ። በራሳችሁ ዐዋቂዎች ነን አትበሉ።
Διαβάστε ወደ ሮሜ ሰዎች 12:16
13
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:20
ነገር ግን ጠላትህ ቢርበው አብላው፤ ቢጠማው አጠጣው፤ ይህን በማድረግህ በራሱ ላይ የእሳት ፍም ትከምራለህና።
Διαβάστε ወደ ሮሜ ሰዎች 12:20
14
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:14-15
የሚያሳድዱአችሁን መርቁ፤ መርቁ እንጂ አትርገሙ። ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችሁ፤ ከሚያለቅሱ ጋር አልቅሱ።
Διαβάστε ወደ ሮሜ ሰዎች 12:14-15
15
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:13
ቅዱሳንን በሚያስፈልጋቸው እርዱ፤ እንግዶችን ተቀበሉ።
Διαβάστε ወደ ሮሜ ሰዎች 12:13
16
ወደ ሮሜ ሰዎች 12:4-5
በአንድ አካል ብዙ የሰውነት ክፍሎች እንዳሉን፥ የሰውነት ክፍሎቹም ሥራ አንድ እንዳልሆነ ሁሉ፥ እንዲሁም ብዙዎች ስንሆን በክርስቶስ አንድ አካል ነን፥ እርስ በእርሳችንም እያንዳንዳችን የሌላው የሰውነት ክፍሎች ነን።
Διαβάστε ወደ ሮሜ ሰዎች 12:4-5
Αρχική
Αγία Γραφή
Σχέδια
Βίντεο