1
ኦሪት ዘፀአት 20:2-3
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መቅካእኤ
“ከግብጽ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣሁህ ጌታ አምላክህ እኔ ነኝ። “ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይኑሩህ።
Σύγκριση
Διαβάστε ኦሪት ዘፀአት 20:2-3
2
ኦሪት ዘፀአት 20:4-5
በላይ በሰማያት ካለው፥ በታች በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር የማናቸውንም አምሳል፥ የተቀረጸ ምስል ለአንተ አታድርግ። አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውም፤ እኔ ጌታ አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኃጢአት በልጆች ላይ የማመጣ፥
Διαβάστε ኦሪት ዘፀአት 20:4-5
3
ኦሪት ዘፀአት 20:12
“ጌታ አምላክህ በሚሰጥህ ምድር ዕድሜህ እንዲረዝም፥ አባትህንና እናትህን አክብር።
Διαβάστε ኦሪት ዘፀአት 20:12
4
ኦሪት ዘፀአት 20:8
“እንድትቀድሰው የሰንበትን ቀን አስታውስ።
Διαβάστε ኦሪት ዘፀአት 20:8
5
ኦሪት ዘፀአት 20:7
“የጌታ የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ፤ ጌታ ስሙን በከንቱ የሚጠራውን ሳይቀጣው አያልፍም።
Διαβάστε ኦሪት ዘፀአት 20:7
6
ኦሪት ዘፀአት 20:9-10
ስድስት ቀን ሥራህን ሥራ፥ ተግባርህንም ሁሉ ፈጽም፤ ሰባተኛው ቀን ግን ለጌታ አምላክህ ሰንበት ነው፤ አንተ፥ ወንድ ልጅህ፥ ሴት ልጅህ፥ ወንድ ሠራተኛህ፥ ሴት ሠራተኛህ፥ ከብትህ፥ በደጆችህም ውስጥ ያለ መጻተኛ ሁሉ በእርሱ ምንም ሥራ አትሥሩ፤
Διαβάστε ኦሪት ዘፀአት 20:9-10
7
ኦሪት ዘፀአት 20:17
“የባልንጀራህን ቤት አትመኝ፤ የባልንጀራህን ሚስት፥ ወንድ ሠራተኛውን፥ ሴት ሠራተኛውን፥ በሬውን፥ አህያውን፥ የባልንጀራህ የሆነውን ሁሉ ማናቸውንም አትመኝ።”
Διαβάστε ኦሪት ዘፀአት 20:17
8
ኦሪት ዘፀአት 20:16
“በባልንጀራህ ላይ በሐሰት አትመስክር።
Διαβάστε ኦሪት ዘፀአት 20:16
9
ኦሪት ዘፀአት 20:14
“አታመንዝር።
Διαβάστε ኦሪት ዘፀአት 20:14
10
ኦሪት ዘፀአት 20:13
“አትግደል።
Διαβάστε ኦሪት ዘፀአት 20:13
11
ኦሪት ዘፀአት 20:15
“አትስረቅ።
Διαβάστε ኦሪት ዘፀአት 20:15
Αρχική
Αγία Γραφή
Σχέδια
Βίντεο