ሩት 2:22 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ
ሩት 2:22 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
ኑኃሚንም ምራቷን ሩትን፣ “የእኔ ልጅ፤ እንዲህ ካልሽማ ከሴት ሠራተኞቹ ጋራ ዐብሮ መሄድ ይሻልሻል፤ ወደ ሌላ ሰው አዝመራ ብትሄጂ ጕዳት ሊያገኝሽ ይችላልና” አለቻት።
ሩት 2:22 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
ናዖሚም “እውነት ነው ልጄ፤ በቦዔዝ እርሻ ካሉት ሴቶች ጋር ሆነሽ ብትቃርሚ ይሻልሻል፤ ወደ ሌላ ሰው እርሻ ብትሄጂ ግን ምናልባት ጐልማሶች ያስቸግሩሻል” አለቻት።
ሩት 2:22 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
ኑኃሚንም ምራትዋን ሩትን፦ ልጄ ሆይ፥ ከገረዶቹ ጋር ብትወጪ፥ በሌላም እርሻ ባያገኙሽ መልካም ነው አለቻት።
ሩት 2:22 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))
ሚኃሚንም ምራትዋን ሩትን “ልጄ ሆይ! ከገረዶቹ ጋር ብትወጪ፥ በሌላም እርሻ ባያገኙሽ መልካም ነው፤” አለቻት።
ሩት 2:22 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
ናዖሚም ምራትዋን ሩትን፦ “ልጄ ሆይ፥ ከሴት አገልጋዮቹ ጋር ብትወጪ ይሻላል፥ በሌላም እርሻ ባያገኙሽ መልካም ነው” አለቻት።