ሩት 2:19 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ
ሩት 2:19 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
ዐማቷም፣ “ዛሬ የቃረምሽው ከየት ነው? የትስ ቦታ ስትሠሪ ዋልሽ? መልካም ነገር ያደረገልሽ ሰው የተባረከ ይሁን” አለቻት። ከዚያም ሩት ስትሠራ ስለ ዋለችበት ስፍራ ባለቤት ለዐማቷ ነገረቻት፤ እርሷም፣ “ዛሬ ስቃርም የዋልሁበት አዝመራ ባለቤት፣ ስሙ ቦዔዝ ይባላል” አለቻት።
ሩት 2:19 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
ዐማትዋ “ዛሬ ከየት ቃረምሽ? ወደየትስ ሠራሽ? ይህን መልካም አቀባበል ያደረገልሽን ሰው እግዚአብሔር ይባርከው!” አለቻት። ሩትም “እኔ ስቃርም የዋልኩበት እርሻ ባለቤት ቦዔዝ የሚባል ሰው ነው” ብላ ለናዖሚ ነገረቻት።
ሩት 2:19 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
አማትዋም፦ ዛሬ ወዴት ቃረምሽ? ወዴትስ ሠራሽ? የተቀበለሽ የተባረከ ይሁን አለቻት። እርስዋም፦ ዛሬ የሠራሁበት ሰው ስም ቦዔዝ ይባላል ብላ በማን ዘንድ እንደ ሠራች ለአማትዋ ነገረቻት።
ሩት 2:19 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))
አማትዋም “ዛሬ ወዴት ቃረምሽ? ወዴትስ ሠራሽ? የተቀበለሽ የተባረከ ይሁን፤” አለቻት። እርስዋም “ዛሬ የሠራሁበት ሰው ስም ቦዔዝ ይባላል፤” ብላ በማን ዘንድ እንደ ሠራች ለአማትዋ ነገረቻት።
ሩት 2:19 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
አማትዋም፦ “ዛሬ ከየት ቃረምሽ? ወዴትስ ሠራሽ? የተቀበለሽ የተባረከ ይሁን” አለቻት። እርሷም፦ “ዛሬ የሠራሁበት ሰው ስም ቦዔዝ ይባላል” ብላ በማን ዘንድ እንደ ሠራች ለአማቷ ነገረቻት።