ሮሜ 7:4 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ

ሮሜ 7:4 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

ስለዚህ ወንድሞቼ ሆይ፤ እናንተም በክርስቶስ ኢየሱስ ሥጋ ለሕግ ሞታችኋል፤ ይህም ከሙታን ለተነሣው ለርሱ፣ ለሌላው ሆናችሁ ለእግዚአብሔር ፍሬ እንድናፈራ ነው።

ያጋሩ
ሮሜ 7 NASV

ሮሜ 7:4 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ወንድሞቼ ሆይ፥ የእናንተም ሁኔታ እንደዚሁ ነው፤ እናንተ የክርስቶስ አካል ክፍል ስለ ሆናችሁ በሞት የመለየትን ያኽል ከሕግ ተለይታችኋል፤ ስለዚህ ለእግዚአብሔር አገልግሎት ፍሬ እንድናፈራ ከሞት የተነሣው የክርስቶስ ወገኖች ሆናችኋል።

ሮሜ 7:4 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

ወን​ድ​ሞች ሆይ! እና​ንተ እን​ዲሁ የክ​ር​ስ​ቶስ አካል ስለ ሆና​ችሁ ከኦ​ሪት ተለ​ይ​ታ​ች​ኋል፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፍሬ እን​ድ​ታ​ፈሩ ከሙ​ታን ተለ​ይቶ ለተ​ነ​ሣው ለዳ​ግ​ማዊ አዳም ሆና​ች​ኋል።

ሮሜ 7:4 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

እንዲሁ፥ ወንድሞቼ ሆይ፥ እናንተ ደግሞ በክርስቶስ ሥጋ ለሕግ ተገድላችኋል፤ ለእግዚአብሔር ፍሬ እንድናፈራ፥ እናንተ ለሌላው፥ ከሙታን ለተነሣው፥ ለእርሱ ትሆኑ ዘንድ።

ሮሜ 7:4 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

ስለዚህ ወንድሞቼ ሆይ! እናንተ ደግሞ በክርስቶስ ሥጋ ለሕግ ተገድላችኋል፤ እናንተ ለሌላው፥ ከሙታን ለተነሣው፥ ለእርሱ እንድትሆኑና ለእግዚአብሔር ፍሬ እንድናፈራ ነው።