Skip to content
የBible App ዓርማ

ሮሜ 5:14 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ

ሮሜ 5:14 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

ይሁን እንጂ ከአዳም ጀምሮ እስከ ሙሴ ድረስ ባሉት፣ እንደ አዳም ሕግን በመጣስ ኀጢአት ባልሠሩት ላይ እንኳ ሞት ነገሠ፤ አዳም ይመጣ ዘንድ ላለው አምሳሉ ነበረ።

ያጋሩ
ሮሜ 5 NASV

ሮሜ 5:14 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ሆኖም እንደ አዳም ሕግን በመተላለፍ ኃጢአት ባልሠሩት ላይ እንኳ ሳይቀር ሞት ከአዳም አንሥቶ እስከ ሙሴ ድረስ በሰው ሁሉ ላይ ሥልጣን አገኘ። ይህ አዳም ወደፊት ለሚመጣው ክርስቶስ ምሳሌ ነበረ።

ሮሜ 5:14 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

ነገር ግን በአ​ዳም ኀጢ​አት ምክ​ን​ያት ከአ​ዳም እስከ ሙሴ የበ​ደ​ሉ​ት​ንም ያል​በ​ደ​ሉ​ት​ንም ሞት ገዛ​ቸው፤ ሁሉ በአ​ዳም አም​ሳል ተፈ​ጥ​ሮ​አ​ልና፥ አዳ​ምም ይመጣ ዘንድ ላለው ለእ​ርሱ አም​ሳሉ ነውና።

ሮሜ 5:14 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

ነገር ግን በአዳም መተላለፍ ምሳሌ ኃጢአትን ባልሠሩት ላይ እንኳ፥ ከአዳም ጀምሮ እስከ ሙሴ ድረስ ሞት ነገሠ፤ አዳም ይመጣ ዘንድ ላለው ለእርሱ አምሳሉ ነውና።

ሮሜ 5:14 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

ነገር ግን ለሚመጣው ምሳሌ እንደነበረው እንደ አዳም ሕግን ባልተላለፉት ላይ እንኳ፥ ከአዳም ጀምሮ እስከ ሙሴ ድረስ ሞት ነገሠ።