Skip to content
የBible App ዓርማ

ሮሜ 15:8 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ

ሮሜ 15:8 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

ለአባቶች የተሰጠውን የተስፋ ቃል ያጸና ዘንድ ለእግዚአብሔር እውነት ሲል ክርስቶስ የአይሁድ አገልጋይ እንደ ሆነ እነግራችኋለሁና፤

ሮሜ 15:8 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ይህንንም ስናገር እግዚአብሔር ለቀደሙት አባቶች የሰጠው ተስፋ እንዲፈጸምና የእግዚአብሔርም እውነተኛነት እንዲታወቅ ክርስቶስ የአይሁድ አገልጋይ ሆነ ማለቴ ነው።

ሮሜ 15:8 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

እን​ግ​ዲህ ክር​ስ​ቶስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል እው​ነት ለማ​ድ​ረግ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ን​ንም ተስፋ ያጸና ዘንድ ለግ​ዝ​ረት መል​እ​ክ​ተና ሆነ እላ​ለሁ።

ሮሜ 15:8-9 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

ለአባቶች የተሰጠውን የተስፋ ቃል ያጸና ዘንድ ደግሞም፦ ስለዚህ በአሕዛብ መካከል አመሰግንሃለሁ ለስምህም እዘምራለሁ ተብሎ እንደ ተጻፈ፥ አሕዛብ ስለ ምሕረቱ እግዚአብሔርን ያከብሩ ዘንድ፥ ክርስቶስ ስለ እግዚአብሔር እውነት የመገረዝ አገልጋይ ሆነ እላለሁ።

ሮሜ 15:8 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

ለአባቶች የተሰጠውን የተስፋ ቃል ሊያጸና፤ ስለ እግዚአብሔር እውነት ክርስቶስ ለተገረዙት አገልጋይ ሆነ እላለሁ፤