Skip to content

ሮሜ 15:27 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ

ሮሜ 15:27 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

ርዳታ ለማድረግ ወድደዋል፤ በርግጥም ባለዕዳዎቻቸው ናቸው። አሕዛብ የአይሁድ መንፈሳዊ በረከት ተካፋዮች ከሆኑ፣ ያገኙትን ምድራዊ በረከት ከአይሁድ ጋራ ይካፈሉ ዘንድ የእነርሱ ባለዕዳዎች ናቸው።

ሮሜ 15:27 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ይህንንም ርዳታ በፈቃደኛነት የለገሡት ግዴታቸው በመሆኑ ነው፤ አሕዛብ ከአይሁድ ጋር የመንፈስ በረከት ተካፋዮች ከሆኑ እነርሱም በሥጋዊ በረከታቸው አይሁድን የመርዳት ግዴታ አለባቸው።

ሮሜ 15:27 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

የሚ​ገ​ባ​ቸ​ውም ሰለ​ሆነ በመ​ን​ፈ​ሳዊ ሥራ አሕ​ዛ​ብን ከተ​ባ​በ​ሩ​አ​ቸው ለሰ​ው​ነ​ታ​ቸው በሚ​ያ​ስ​ፈ​ል​ጋ​ቸው ሊረ​ዱ​አ​ቸው ይገ​ባል።

ሮሜ 15:27 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

ወደዋልና፥ የእነርሱም ባለ ዕዳዎች ናቸው፤ አሕዛብ በእነርሱ መንፈሳዊ ነገርን ተካፋዮች ከሆኑ በሥጋዊ ነገር ደግሞ ያገለግሉአቸው ዘንድ ይገባቸዋልና።

ሮሜ 15:27 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

ተደስተዋልና የእነርሱ ባለ ዕዳዎች ናቸው፤ በእነርሱ መንፈሳዊ ነገር አሕዛብ ተካፋዮች ከሆኑ በሥጋዊ ነገር ደግሞ ሊያገለግሉአቸው ይገባቸዋል።