Skip to content

ሮሜ 15:26 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ

ሮሜ 15:26 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

ምክንያቱም መቄዶንያና አካይያ፣ በኢየሩሳሌም ካሉት ቅዱሳን መካከል የሚገኙትን ድኾች ለመርዳት ተነሣሥተዋልና።

ሮሜ 15:26 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ይኸውም የመቄዶንያና በአካይያ የሚገኙ የእግዚአብሔር ወገኖች በኢየሩሳሌም ላሉት ድኾች የገንዘብ ርዳታ ለመላክ በፈቃዳቸው ስለ ወሰኑ ነው።

ሮሜ 15:26 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

መቄ​ዶ​ን​ያና አካ​ይያ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቅዱ​ሳን መካ​ከል ላሉ ድሆች አስ​ተ​ዋ​ጽ​ፅኦ ለማ​ድ​ረግ ተባ​ብ​ረ​ዋ​ልና።

ሮሜ 15:26 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

መቄዶንያና አካይያ በኢየሩሳሌም ቅዱሳን መካከል ያሉትን ድሆች ይረዱ ዘንድ ወደዋልና።

ሮሜ 15:26 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

መቄዶንያና አካይያ በኢየሩሳሌም ካሉት ቅዱሳን መካከል ያሉትን ድሆች ለመርዳት ወደዋል።