Skip to content
የBible App ዓርማ

ሮሜ 13:3 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ

ሮሜ 13:3 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

ገዦች ክፉ ለሚሠሩ እንጂ መልካም ለሚያደርጉ የሚያስፈሩ አይደሉምና። ባለሥልጣንን እንዳትፈራ ትፈልጋለህን? እንግዲያስ መልካሙን አድርግ፤ እርሱም ያመሰግንሃል፤

ሮሜ 13:3 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ገዢዎች የሚያስፈሩት ክፉ አድራጊዎችን እንጂ መልካም አድራጊዎችን አይደለም፤ ባለሥልጣንን እንዳትፈራ ትፈልጋለህን? እንግዲያውስ መልካሙን ነገር አድርግ፤ ከእርሱም ምስጋናን ታገኛለህ።

ሮሜ 13:3 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

ሹሞች ሥራው ክፉ ለሆነ ሰው እንጂ መል​ካም ለሚ​ሠራ የሚ​አ​ስ​ፈሩ አይ​ደ​ሉም፤ ሹሞ​ችን እን​ዳ​ት​ፈራ ብት​ፈ​ልግ መል​ካም አድ​ርግ፤ እነ​ርሱ ደግሞ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ሃል፤

ሮሜ 13:3 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

ገዥዎች ለክፉ አድራጊዎች እንጂ መልካም ለሚያደርጉ የሚያስፈሩ አይደሉምና። ባለ ሥልጣንን እንዳትፈራ ትወዳለህን? መልካሙን አድርግ ከእርሱም ምስጋና ይሆንልሃል፤

ሮሜ 13:3 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

ገዢዎች ለክፉ አድራጊዎች እንጂ መልካም ለሚያደርጉ የሚያስፈሩ አይደሉምና። ባለ ሥልጣንን እንዳትፈራ ትወዳለህን? መልካሙን አድርግ፤ ከእርሱም ምስጋናን ታገኛለህ፤