Skip to content

ሮሜ 11:11 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ

ሮሜ 11:11 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

ተመልሰው እስከማይድኑ ድረስ ተሰናከሉን? ብዬ እንደ ገና እጠይቃለሁ፤ ከቶ አይሆንም! ይልቁንም እስራኤልን ለማስቀናት ሲባል በእነርሱ መተላለፍ ምክንያት ድነት ለአሕዛብ መጥቷል።

ሮሜ 11:11 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

እስቲ፥ እንደገና ልጠይቅ፤ አይሁድ የወደቁት ዳግመኛ እንደማይነሡ ሆነው ነውን? አይደለም! በአይሁድ በደል ምክንያት አሕዛብ መዳንን አገኙ፤ ይህም የሆነው አይሁድ በአሕዛብ እንዲቀኑ ለማድረግ ነው።

ሮሜ 11:11 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

እን​ግ​ዲህ እላ​ለሁ፤ ሊወ​ድቁ ተሰ​ና​ከ​ሉን? አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን እስ​ራ​ኤል ይቀኑ ዘንድ እነ​ርሱ በመ​ሰ​ና​ከ​ላ​ቸው ለአ​ሕ​ዛብ ድኅ​ነት ሆነ።

ሮሜ 11:11 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

እንግዲህ፦ የተሰናከሉ እስኪወድቁ ድረስ ነውን? እላለሁ። አይደለም፤ ነገር ግን እነርሱን ያስቀናቸው ዘንድ በእነርሱ በደል መዳን ለአሕዛብ ሆነ።

ሮሜ 11:11 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

ተመልሰው መዳን እስከማይችሉ ድረስ ተሰናከሉን? ብዬ እጠይቃለሁ፤ በጭራሽ! ነገር ግን እነርሱን ለማስቀናት፥ በእነርሱ በደል፥ መዳን ለአሕዛብ ሆነ።