Skip to content
የBible App ዓርማ

ሮሜ 10:16 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ

ሮሜ 10:16 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

ነገር ግን የሰሙት ሁሉ የምሥራቹን ቃል አልተቀበሉም፤ ኢሳይያስም፣ “ጌታ ሆይ፤ መልእክታችንን ማን አምኗል?” ብሏልና።

ሮሜ 10:16 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ነገር ግን ኢሳይያስ፥ “ጌታ ሆይ! የተናገርነውን ቃል ማን ተቀበለ” ብሎ እንደ ተናገረ፥ ሁሉም የምሥራቹን ቃል አልተቀበሉም።

ሮሜ 10:16 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

ነገር ግን ሁሉም የወ​ን​ጌ​ልን ትም​ህ​ርት የሰሙ አይ​ደ​ለም፤ ኢሳ​ይ​ያ​ስም፥ “አቤቱ፥ ምስ​ክ​ር​ነ​ታ​ች​ን​ንስ ማን አመነ? የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርስ ክንዱ ለማን ተገ​ለጠ?” ብሎ​አ​ልና።

ሮሜ 10:16 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

ነገር ግን ሁሉ ለምሥራቹ ቃል አልታዘዙም። ኢሳይያስ፦ ጌታ ሆይ፥ ምስክርነታችንን ማን አመነ? ብሎአልና።

ሮሜ 10:16 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

ነገር ግን ሁሉም ለምሥራቹ ቃል አልታዘዙም። ኢሳይያስ “ጌታ ሆይ! የተናገርነውን ማን አመነ?” ብሏልና።