Skip to content
የBible App ዓርማ

ሮሜ 1:26 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ

ሮሜ 1:26 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

በዚህም ምክንያት እግዚአብሔር አሳፋሪ ለሆነ ምኞት አሳልፎ ሰጣቸው፤ ሴቶቻቸውም እንኳ ለባሕርያቸው የሚገባውን ግንኙነት ባሕርያቸው ላልሆነው ግንኙነት ለወጡ።

ያጋሩ
ሮሜ 1 NASV

ሮሜ 1:26 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ሰዎች ይህን በማድረጋቸው ምክንያት እግዚአብሔር ለማይገባ አስነዋሪ ምኞት አሳልፎ ሰጣቸው፤ ሴቶቻቸው እንኳ የተለመደውን ተፈጥሮአዊ ግንኙነት ባልተለመደ ግንኙነት ለወጡት።

ሮሜ 1:26 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

ስለ​ዚ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክፉ መቅ​ሠ​ፍ​ትን አመ​ጣ​ባ​ቸው፤ ሴቶ​ቻ​ቸ​ውም ለባ​ሕ​ር​ያ​ቸው የሚ​ገ​ባ​ውን ትተው ለባ​ሕ​ር​ያ​ቸው የማ​ይ​ገ​ባ​ውን ሠሩ።

ሮሜ 1:26 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

ስለዚህ እግዚአብሔር ለሚያስነውር ምኞት አሳልፎ ሰጣቸው፤ ሴቶቻቸውም ለባሕርያቸው የሚገባውን ሥራ ለባሕርያቸው በማይገባው ለወጡ፤

ሮሜ 1:26 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

በዚህ ምክንያት እግዚአብሔር ለሚያዋርድ ፍትወት አሳልፎ ሰጣቸው፤ ሴቶቻቸውም ተፈጥሮአዊውን ግንኙነት ተፈጥሮአዊ ባልሆነ ግንኙነት ለወጡ፤