ሮሜ 1:1 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ

ሮሜ 1:1 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

ጳውሎስ፣ የክርስቶስ ኢየሱስ ባሪያ፣ ሐዋርያ ሊሆን የተጠራና ለእግዚአብሔር ወንጌል የተለየ፤

ያጋሩ
ሮሜ 1 NASV

ሮሜ 1:1 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ከሆነው፥ ለሐዋርያነት ከተጠራው፥ የእግዚአብሔርንም ወንጌል ለማስተማር ከተመረጠው ከጳውሎስ የተላከ።

ሮሜ 1:1 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ወን​ጌል ለማ​ስ​ተ​ማር ተለ​ይቶ ከተ​ጠራ ሐዋ​ርያ፥ የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ አገ​ል​ጋይ ከሚ​ሆን ከጳ​ው​ሎስ፥

ሮሜ 1:1-2 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

ሐዋርያ ሊሆን የተጠራ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ጳውሎስ በነቢያቱ አፍ በቅዱሳን መጻሕፍት አስቀድሞ ተስፋ ለሰጠው ለእግዚአብሔር ወንጌል ተለየ።

ሮሜ 1:1 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

የክርስቶስ ኢየሱስ ባርያ ጳውሎስ፥ ሐዋርያ ሊሆን የተጠራ፥ ለእግዚአብሔር ወንጌል የተለየ፥