Skip to content
የBible App ዓርማ

ዘኍልቍ 7:3 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ

ዘኍልቍ 7:3 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

ስድስት የተሸፈኑ ሠረገሎችና ዐሥራ ሁለት በሬዎች ይኸውም ከእያንዳንዱ አለቃ አንዳንድ በሬ እንዲሁም ከየሁለቱ አለቆች አንድ ሠረገላ ስጦታ አድርገው ወደ እግዚአብሔር ፊት አመጡ፤ እነዚህንም በማደሪያው ድንኳን ፊት አቀረቧቸው።

ዘኍልቍ 7:3 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

መባቸውን ለእግዚአብሔር አቀረቡ፤ ያቀረቡአቸውም መባዎች በየሁለቱ አለቆች ስም አንድ ሠረገላ፥ እንዲሁም በእያንዳንዱ አለቃ ስም አንድ በሬ ሆኖ፥ ስድስት ሠረገሎችና ዐሥራ ሁለት በሬዎች ነበሩ፤ እነዚህንም መባዎች በመገናኛው ድንኳን ፊት አቀረቡ።

ዘኍልቍ 7:3 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

መባ​ቸ​ው​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አቀ​ረቡ፤ የተ​ከ​ደኑ ስድ​ስት ሰረ​ገ​ሎች ዐሥራ ሁለ​ትም በሬ​ዎች፤ በየ​ሁ​ለ​ቱም አለ​ቆች አንድ ሰረ​ገላ አቀ​ረቡ፤ ሁሉም እያ​ን​ዳ​ንዱ አንድ በሬ በድ​ን​ኳኑ ፊት አቀ​ረቡ።

ዘኍልቍ 7:3 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

መባቸውንም በእግዚአብሔር ፊት አቀረቡ፥ የተከደኑ ስድስት ሰረገሎች አሥራ ሁለትም በሬዎች፤ በየሁለቱም አለቆች አንድ ሰረገላ አቀረቡ፥ ሁሉም እያንዳንዱ አንድ በሬ በማደሪያው ፊት አቀረቡ።

ዘኍልቍ 7:3 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

መባቸውንም በጌታ ፊት አመጡ፥ የተሸፈኑ ስድስት ሰረገሎች ዐሥራ ሁለትም በሬዎች፤ ለሁለትም አለቆች ለእያንዳንዳቸው አንድ ሠረገላ ለእያንዳንዱም አለቃ አንዳንድ በሬ አመጡ፤ በማደሪያው ፊት አቀረቡ።