Skip to content
የBible App ዓርማ

ዘኍልቍ 3:4 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ

ዘኍልቍ 3:4 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

ናዳብና አብዩድ ግን በሲና ምድረ በዳ ባልተፈቀደ እሳት ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ባቀረቡ ጊዜ እዚያው እፊቱ ወድቀው ሞቱ። ወንዶች ልጆች ስላልነበሯቸውም አልዓዛርና ኢታምር ብቻ አባታቸው አሮን በሕይወት በነበረበት ዘመን በክህነት ያገለግሉ ነበር።

ዘኍልቍ 3:4 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ነገር ግን ከእነርሱ ውስጥ ናዳብና አቢሁ በሲና በረሓ በእግዚአብሔር ፊት ያልተቀደሰ እሳት ጭረው በማቅረባቸው ተቀሥፈው ሞቱ፤ እነርሱም ልጆች አልነበሩአቸውም፤ ስለዚህም አልዓዛርና ኢታማር ብቻ አባታቸው አሮን በሕይወት በነበረበት ዘመን ሁሉ በክህነት ያገለግሉ ነበር።

ዘኍልቍ 3:4 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

ናዳ​ብና አብ​ዩድ በሲና ምድረ በዳ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ከሌላ እሳት ጭረው አም​ጥ​ተ​ዋ​ልና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ሞቱ፤ ልጆ​ችም አል​ነ​በ​ሩ​አ​ቸ​ውም። አል​ዓ​ዛ​ርና ኢታ​ምር ከአ​ባ​ታ​ቸው ከአ​ሮን ጋር በክ​ህ​ነት ያገ​ለ​ግሉ ነበር።

ዘኍልቍ 3:4 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

ናዳብና አብዩድ በሲና ምድረ በዳ በእግዚአብሔር ፊት ልዩ እሳት ባቀረቡ ጊዜ በእግዚአብሔር ፊት ሞቱ፤ ልጆችም አልነበሩአቸውም። አልዓዛርና ኢታምር በአባታቸው በአሮን ፊት በክህነት ያገለግሉ ነበር።

ዘኍልቍ 3:4 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

ናዳብና አብዩድ በሲና ምድረ በዳ በጌታ ፊት ያልተፈቀደውን እሳት ባቀረቡ ጊዜ በጌታ ፊት ሞቱ፤ ልጆችም አልነበሩአቸውም። አልዓዛርና ኢታምር በአባታቸው በአሮን ፊት በክህነት ያገለግሉ ነበር።