ዘኍልቍ 2:2 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ

ዘኍልቍ 2:2 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

“እስራኤላውያን ከምስክሩ ድንኳን ትይዩ ዙሪያውን ጥቂት ራቅ ብለው እያንዳንዱ ሰው በየዐርማውና በየቤተ ሰቡ ምልክት ሥር ይስፈር።”

ዘኍልቍ 2:2 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

እስራኤላውያን በየተመደቡበት ቡድን ሰንደቅ ዓላማና በየነገዳቸው ዐርማ ሥር ይሰፍራሉ፤ አሰፋፈራቸውም የመገናኛው ድንኳን በዙሪያው ሆኖ ፊታቸው ከድንኳኑ ትይዩ ይሆናል።

ዘኍልቍ 2:2 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

“የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እያ​ን​ዳ​ንዱ በየ​ሥ​ር​ዐቱ፥ በየ​ዓ​ላ​ማው፥ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች፥ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ዙሪያ አን​ጻር ይስ​ፈሩ።

ዘኍልቍ 2:2 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

የእስራኤል ልጆች እያንዳንዱ በየዓላማው በየአባቶቻቸው ቤቶች ምልክት ይስፈሩ፤ በመገናኛው ድንኳን አፋዛዥ ዙሪያ ይስፈሩ።

ዘኍልቍ 2:2 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

“የእስራኤል ልጆች እያንዳንዱ በየዓላማው በየአባቶቻቸው ቤቶች ምልክት ይስፈሩ፤ በመገናኛው ድንኳን ትይዩ በሁሉም አቅጣጫ ይስፈሩ።