Skip to content

ዘኍልቍ 2:17 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ

ዘኍልቍ 2:17 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

ከዚህ በኋላ የመገናኛው ድንኳንና የሌዋውያን ምድብ በመካከል ሆነው ይጓዛሉ፤ እያንዳንዳቸውም አሰፋፈራቸውን በመከተል ቦታቸውን ጠብቀው በዐርማቸው ሥር ይጓዛሉ።

ዘኍልቍ 2:17 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

በመጀመሪያዎቹ ሁለት ክፍሎችና በመጨረሻዎቹ ሁለት ክፍሎች መካከል ሌዋውያን የመገናኛውን ድንኳን ይዘው ይጓዛሉ፤ እያንዳንዱም ክፍል ሰፈሩ ተለይቶ በሚታወቅበት ዓርማ ሥር ምድብ ተራውን ጠብቆ ይጓዛል።

ዘኍልቍ 2:17 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

“ከዚ​ያም በኋላ የም​ስ​ክሩ ድን​ኳን፥ በሰ​ፈ​ሮ​ቹም መካ​ከል የሌ​ዋ​ው​ያን ወገን ይጓ​ዛል፤ እንደ አሰ​ፋ​ፈ​ራ​ቸው ሰው ሁሉ በየ​ስ​ፍ​ራው፥ በየ​ዓ​ላ​ማ​ውም ይጓ​ዛሉ።

ዘኍልቍ 2:17 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

ከዚያም በኋላ የመገናኛው ድንኳን በሰፈሮቹም መካከል የሌዋውያን ሰፈር ይጓዛል፤ እንደ ሰፈራቸው ሰው ሁሉ በየስፍራው በየዓላማውም ይጓዛሉ።

ዘኍልቍ 2:17 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

“ከዚያም በኋላ በሰፈሮቹም መካከል የመገናኛው ድንኳን ከሌዋውያን ሰፈር ጋር ይጓዛል፤ እንደ ሰፈራቸው እያንዳንዱ ሰው ስፍራቸውን ይዘው በየዓላሞቻቸው ይጓዛሉ።