Skip to content
የBible App ዓርማ

ዘኍልቍ 18:2 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ

ዘኍልቍ 18:2 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

አንተና ልጆችህ በምስክሩ ድንኳን ፊት በምታገለግሉበት ጊዜ ዐብረዋችሁ እንዲሆኑና እንዲረዷችሁ ከአባትህ ነገድ ሌዋውያንን አምጣቸው።

ዘኍልቍ 18:2 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

አንተና ልጆችህ በምስክሩ ድንኳን ፊት በምታገለግሉበት ጊዜ ከእናንተ ጋር በመሥራት ይረዱአችሁ ዘንድ፥ የሌዊ ነገድ የሆኑትን ወገኖችህን ውሰድ፤

ዘኍልቍ 18:2 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

ደግ​ሞም የአ​ባ​ት​ህን የሌ​ዊን ነገድ ወን​ድ​ሞ​ች​ህን ወደ አንተ ሰብ​ስብ፤ ከአ​ን​ተም ጋር በአ​ን​ድ​ነት ይሁኑ፤ ያገ​ል​ግ​ሉ​ህም፤ አንተ ከአ​ን​ተም ጋር ልጆ​ችህ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ፊት ትሆ​ና​ላ​ችሁ።

ዘኍልቍ 18:2 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

ደግሞም የአባትህን የሌዊን ነገድ ወንድሞችህን ከአንተ ጋር አቅርብ፤ ከአንተም ጋር በአንድነት ይሁኑ፥ ያገልግሉህም፤ አንተ ግን ከአንተም ጋር ልጆችህ በምስክሩ ድንኳን ፊት ትሆናላችሁ።

ዘኍልቍ 18:2 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

እንዲሁም አንተ ከአንተም ጋር ልጆችህ በምስክሩ ድንኳን ፊት ሳላችሁ ከአንተ ጋር በአንድነት እንዲሆኑ፥ እንዲያገለግሉህም፥ የአባትህን የሌዊን ነገድ ወንድሞችህን ደግሞ ከአንተ ጋር አምጣቸው።