ዘኍልቍ 10:2 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ
ዘኍልቍ 10:2 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
“ከተቀጠቀጠ ብር ሁለት መለከት አብጅ፤ ማኅበረ ሰቡን ለመጥሪያና ከሰፈራቸው እንዲነሡም ለመቀስቀሻ አድርጋቸው።
ዘኍልቍ 10:2 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
“ሕዝቡን በአንድነት ለመሰብሰብም ሆነ ከሰፈር ለመቀስቀስ የሚያገለግሉ ሁለት መለከቶችን ከተቀጠቀጠ ብር ሥራ።
ዘኍልቍ 10:2 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
“ሁለት የብር መለከቶች አስጠፍጥፈህ ለአንተ አድርግ፤ ማኅበሩን ለመጥራት ከሰፈራቸውም ለማስጓዝ ይሁኑልህ።
ዘኍልቍ 10:2 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))
ሁለት የብር መለከቶች አጠፍጥፈህ ለአንተ አድርግ፤ ማኅበሩን ለመጥራት ከሰፈራቸውም ለማስጓዝ ይሁኑልህ።
ዘኍልቍ 10:2 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
“ሁለት የብር መለከቶች ሥራ፤ እነርሱንም ተቀጥቅጦ በሚሠራ ሥራ ለራስህ አብጃቸው፤ ማኅበሩን ለመጥራት ከሰፈራቸውም ተነሥተው እንዲጓዙ ለመቀስቀስ ተጠቀምባቸው።