Skip to content
የBible App ዓርማ

ማቴዎስ 9:14 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ

ማቴዎስ 9:14 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

የመጥምቁ ዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ወደ ኢየሱስ ቀርበው፣ “እኛና ፈሪሳውያን ስንጾም፣ የአንተ ደቀ መዛሙርት ግን ለምን አይጾሙም?” ብለው ጠየቁት።

ማቴዎስ 9:14 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

በዚያን ጊዜ፥ የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ወደ ኢየሱስ መጥተው፥ “እኛና ፈሪሳውያን ዘወትር እንጾማለን፤ የአንተ ደቀ መዛሙርት ግን የማይጾሙት ለምንድን ነው?” ሲሉ ጠየቁት።

ማቴዎስ 9:14 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

በዚያን ጊዜ የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ወደ እርሱ ቀርበው “እኛና ፈሪሳውያን ብዙ ጊዜ የምንጦመው፥ ደቀ መዛሙርትህ ግን የማይጦሙት ስለ ምንድር ነው?” አሉት።

ማቴዎስ 9:14 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

በዚያን ጊዜ የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ወደ እርሱ ቀርበው፦ እኛና ፈሪሳውያን፥ ብዙ ጊዜ የምንጦመው፥ ደቀ መዛሙርትህ ግን የማይጦሙት ስለ ምንድር ነው? አሉት።

ማቴዎስ 9:14 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

በዚያን ጊዜ የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ወደ እርሱ መጥተው “እኛና ፈሪሳውያን ብዙ ጊዜ እንጾማለን፥ ደቀ መዛሙርትህ ግን የማይጾሙት ለምንድን ነው?” አሉት።