ማቴዎስ 8:17 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ
ማቴዎስ 8:17 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
በዚህም ኢሳይያስ እንዲህ ብሎ የተናገረው ትንቢት ተፈጸመ፤ “እርሱ ደዌያችንን ወሰደ፤ ሕመማችንንም ተሸከመ።”
ያጋሩ
ማቴዎስ 8 NASVማቴዎስ 8:17 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
ይህንንም በማድረጉ በነቢዩ ኢሳይያስ፥ “እርሱ ደዌአችንን ተቀበለ፤ ሕመማችንንም ተሸከመ” የተባለው ትንቢት ተፈጸመ።
ያጋሩ
ማቴዎስ 8 አማ05ማቴዎስ 8:16-17 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
በመሸም ጊዜ አጋንንት ያደረባቸውን ብዙዎችን ወደ እርሱ አመጡ፤ በነቢዩ በኢሳይያስ “እርሱ ድካማችንን ተቀበለ ደዌያችንንም ተሸከመ፤” የተባለው ይፈጸም ዘንድ መናፍስትን በቃኣሉ አወጣ፤ የታመሙትንም ሁሉ ፈወሰ።
ማቴዎስ 8:16-17 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))
በመሸም ጊዜ አጋንንት ያደረባቸውን ብዙዎችን ወደ እርሱ አመጡ፤ በነቢዩ በኢሳይያስ፦ እርሱ ድካማችንን ተቀበለ ደዌያችንንም ተሸከመ የተባለው ይፈጸም ዘንድ መናፍስትን በቃኣሉ አወጣ፥ የታመሙትንም ሁሉ ፈወሰ።
ያጋሩ
ማቴዎስ 8 አማ54ማቴዎስ 8:17 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
ይህም በነቢዩ ኢሳይያስ “እርሱ ድካማችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸከመ፤” የተባለው እንዲፈጸም ነው።
ያጋሩ
ማቴዎስ 8 መቅካእኤ