ማቴዎስ 26:73 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ

ማቴዎስ 26:73 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

ከጥቂት ጊዜ በኋላ፣ በዚያ ቆመው የነበሩት ሰዎች ቀርበው ጴጥሮስን፣ “አነጋገርህ ስለሚያጋልጥህ፣ በርግጥ አንተም ከእነርሱ አንዱ ነህ” አሉት።

ማቴዎስ 26:73 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ከጥቂት ጊዜ በኋላ እዚያ ቆመው የነበሩ ሰዎች ወደ ጴጥሮስ ጠጋ ብለው፦ “አነጋገርህ ያስታውቃል፤ በእርግጥ አንተም ከእነርሱ አንዱ ነህ” አሉት።

ማቴዎስ 26:73 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

ጥቂትም ቈይተው በዚያ ቆመው የነበሩ ቀርበው ጴጥሮስን “አነጋገርህ ይገልጥሃልና፥ በእውነት አንተ ደግሞ ከእነርሱ ወገን ነህ፤” አሉት።

ማቴዎስ 26:73 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

ጥቂትም ቍኦይተው በዚያ ቆመው የነበሩ ቀርበው ጴጥሮስን፦ አነጋገርህ ይገልጥሃልና በእውነት አንተ ደግሞ ከእነርሱ ወገን ነህ አሉት።

ማቴዎስ 26:73 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

ከጥቂት ጊዜ በኋላ በዚያ ቆመው የነበሩት ጠጋ ብለው ጴጥሮስን “በእውነት አንተም ከእነርሱ ወገን ነህ፤ አነጋገርህ ያስታውቅብሃልና” አሉት።