Skip to content
የBible App ዓርማ

ማቴዎስ 24:32 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ

ማቴዎስ 24:32 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

“ምሳሌውን ከበለስ ተማሩ፤ ቅርንጫፏ ሲለመልም፣ ቅጠሏ ሲያቈጠቍጥ፣ ያን ጊዜ በጋ እንደ ተቃረበ ታውቃላችሁ።

ማቴዎስ 24:32 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

“የበለስ ዛፍ ምሳሌ ትምህርት ይሁናችሁ፤ ቅርንጫፎችዋ ሲያቈጠቊጡና ቅጠሎችዋም ሲለመልሙ፥ ያ ጊዜ በጋ መቅረቡን ታውቃላችሁ።

ማቴዎስ 24:32 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

“ምሳሌውንም ከበለስ ተማሩ፤ ጫፍዋ ሲለሰልስ ቅጠልዋም ሲያቍኦጠቍጥ፥ ያን ጊዜ በጋ እንደ ቀረበ ታውቃላችሁ፤

ማቴዎስ 24:32 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

ምሳሌውንም ከበለስ ተማሩ፤ ጫፍዋ ሲለሰልስ ቅጠልዋም ሲያቍኦጠቍጥ፥ ያን ጊዜ በጋ እንደ ቀረበ ታውቃላችሁ፤

ማቴዎስ 24:32 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

“ምሳሌውን ከበለስ ዛፍ ተማሩ፤ ቅርጫፍዋ ሲለሰልስ ቅጠሎችዋም ሲያቆጠቁጡ፥ ያንጊዜ በጋ እንደ ቀረበ ታውቃላችሁ፤