Skip to content
የBible App ዓርማ

ማቴዎስ 21:2 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ

ማቴዎስ 21:2 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

እንዲህ አላቸው “በፊታችሁ ወዳለው መንደር ሂዱ፤ እንደ ደረሳችሁም አንዲት አህያ ከነውርንጫዋ ታስራ ታገኛላችሁ፤ ፈትታችሁም ወደ እኔ አምጧቸው።

ማቴዎስ 21:2 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

“በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሂዱ፤ እዚያም አንዲት የታሰረች አህያ ከነውርንጫዋ ወዲያውኑ ታገኛላችሁ፤ ፈትታችሁ አምጡልኝ።

ማቴዎስ 21:2 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

እንዲህም አላቸው “በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሂዱ፤ በዚያን ጊዜም የታሰረችን አህያ ውርንጫም ከእርስዋ ጋር ታገኛላችሁ፤ ፈትታችሁ አምጡልኝ።

ማቴዎስ 21:2 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

እንዲህም አላቸው፦ በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሂዱ፥ በዚያን ጊዜም የታሰረችን አህያ ውርንጫም ከእርስዋ ጋር ታገኛላችሁ፤ ፈትታችሁ አምጡልኝ።

ማቴዎስ 21:2 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

እንዲህም አላቸው “በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሂዱ፤ በዚያን ጊዜ የታሰረች አህያ ከነውርንጫዋ ታገኛላችሁ፤ ፈትታችሁ አምጡልኝ።