ማቴዎስ 2:2-3 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ
ማቴዎስ 2:2-3 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
“የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? በምሥራቅ ኮከቡን አይተን ልንሰግድለት መጥተናልና” ሲሉ ጠየቁ። ንጉሡ ሄሮድስ ይህን በሰማ ጊዜ ታወከ፤ እንዲሁም መላዪቱ ኢየሩሳሌም ዐብራ ታወከች።
ያጋሩ
ማቴዎስ 2 NASVማቴዎስ 2:2-3 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
እንዲህም እያሉ ጠየቁ፦ “የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ የት ነው? ኮከቡን በምሥራቅ አይተን ለእርሱ ልንሰግድለት መጥተናል።” ንጉሡ ሄሮድስ ይህን ነገር በሰማ ጊዜ ደነገጠ፤ የኢየሩሳሌምም ሰዎች ሁሉ ከእርሱ ጋር ደነገጡ።
ያጋሩ
ማቴዎስ 2 አማ05ማቴዎስ 2:1-3 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
ኢየሱስም በይሁዳ ቤተ ልሔም በንጉሡ በሄሮድስ ዘመን በተወለደ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሰብአ ሰገል “የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? ኮከቡን በምሥራቅ አይተን ልንሰግድለት መጥተናልና” እያሉ ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም መጡ። ንጉሡ ሄሮድስም ሰምቶ ደነገጠ፤ ኢየሩሳሌምም ሁሉ ከእርሱ ጋር፤
ማቴዎስ 2:1-3 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))
ኢየሱስም በይሁዳ ቤተ ልሔም በንጉሡ በሄሮድስ ዘመን በተወለደ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሰብአ ሰገል፦ የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? ኮከቡን በምሥራቅ አይተን ልንሰግድለት መጥተናልና እያሉ ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም መጡ። ንጉሡ ሄሮድስም ሰምቶ ደነገጠ፥ ኢየሩሳሌምም ሁሉ ከእርሱ ጋር፤
ያጋሩ
ማቴዎስ 2 አማ54ማቴዎስ 2:2-3 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
እንዲህም አሉ፦ “የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? ኮከቡን በምሥራቅ አይተን ልንሰግድለት መጥተናልና።” ንጉሡ ሄሮድስ ሰምቶ ታወከ፤ መላዋ ኢየሩሳሌምም ከእርሱ ጋር ታወከች፤
ያጋሩ
ማቴዎስ 2 መቅካእኤ